የታላቁ ህዳሴ ግድብ አጭር የፅሁፍ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያ 3ኛ ዙር ሁለተኛ ተሸላሚ መኪናቸውን ተረከቡ - መነሻ - am

嵌套Portlet

资源发布器

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ 星期五, 17 六月 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች 星期三, 8 六月 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ 星期三, 8 六月 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

资源发布器

የታላቁ ህዳሴ ግድብ አጭር የፅሁፍ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያ 3ኛ ዙር ሁለተኛ ተሸላሚ መኪናቸውን ተረከቡ

አዲስ አበባ ጥቅምት 12 2013 (ኤፍ..) የታላቁ ህዳሴ ግድብ አጭር የፅሁፍ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያ 3 ዙር ሁለተኛ ተሸላሚ መኪናቸውን ተረከቡ፡፡

አሸናፊዋ ወይዘሮ አሰፋሽ አፈወርቅ ከኢሉባቡር በቾ ወረዳ ሲሆኑ ዘመናዊ ቢዋይ መኪና ተረክበዋል።

የስልክ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያው የተጀመረው ባሳለፍነው አመት የካቲት ወር ላይ ሲሆን÷ በዚህም 67 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉ ተገልጿል።

በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የቀድሞ የምድር ጦር ሰራዊት አባላትና የሲቪል ሰራተኞች ማህበር የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ አባላት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል 10 ሺህ ብር ስጦታ አበርክተዋል።

ስጦታውን ያስረከቡት የቀድሞ የምድር ጦር ሰራዊት አባላት ድጋፋቸው ቀጣይ እንደሚሆንና ሁሉም ባለው አቅም ለህዳሴ ግድብ አሻራውን እንዲያኖር ጥሪ አቅርበዋል።

የግድቡ የመጀመሪያው የውሃ ሙሌት ከተካሄደ በኋላ የህዝቡ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉም በዚህ ወቅት ተገልጿል።

በመስከረም ወር ብቻም 197 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉና ይህም ከእስካሁኑ ከፍተኛ መሆኑ ተጠቁሟል።

#FBC

嵌套Portlet

资源发布器