ትስስር ለሕዳሴ ግድብ ጥምረት ተመሰረተ - መነሻ - am

嵌套Portlet

资源发布器

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ 星期五, 17 六月 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች 星期三, 8 六月 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ 星期三, 8 六月 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

资源发布器

ትስስር ለሕዳሴ ግድብ ጥምረት ተመሰረተ

ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በቅንጅት የሚሰራ “ትስስር ለሕዳሴ ግድብ” የተሰኘ ጥምረት በይፋ ተመሰረተ።

ጥምረቱ ስለ ዓባይ ግድብ ያለውን እውነታ ለዓለም ማህበረሰብ ለማስረዳት የሚሰራ ሲሆን በሃገር ውስጥና በውጭ ያሉ ምሁራንና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሚናቸውን የሚወጡበት መሆኑን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ ተናግረዋል።
የሙያ ማህበራት፣ የሃይማኖት ተቋማትና የፖለቲካ ፓርቲዎች አባሎቻቸውንና ተከታዮቻቸውን በማስተባበር ለሕዳሴ ግድቡ ድምጽ እንዲሆኑ አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችሉበት እንደሆነም አክለዋል።

ኢትዮጵያውያንን በአንድ አጀንዳ የሚያሰባስበው ጥምረቱ ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ የሚያስችላቸው መሆኑንም ገልጸዋል።

አባቶች መስዋዕትነት ከፍለው ሃገሪቷን አስረክበውናልያሉት ዶክተር አረጋዊ፤እኛም ለቀጣዩ ትውልድ ግድቡን አጠናቀን በማስተላለፍ ታሪክ ማኖር አለብንብለዋል።

ጥምረቱ 12 አባላት ያሉት አስተባባሪ ኮሚቴ ያለው ሲሆን ሃብት አሰባሰብ፣ አካባቢ ጥበቃ፣ ህዝባዊ ዲፕሎማሲ እንዲሁም መገናኛ ብዙሃንና ተግባቦትን ያካተተ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

ምንጭ፡- ኤፍ ሲ፤ ሰኔ 12 2013

嵌套Portlet

资源发布器