ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከጠ/ሚ ዐቢይ የተላከ ደብዳቤን ለኡጋንዳው ፕሬዚዳንት አደረሱ - መነሻ - am

嵌套Portlet

资源发布器

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ 星期五, 17 六月 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች 星期三, 8 六月 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ 星期三, 8 六月 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

资源发布器

ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከጠ/ሚ ዐቢይ የተላከ ደብዳቤን ለኡጋንዳው ፕሬዚዳንት አደረሱ

የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተላከ ደብዳቤን ለዑጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ አደረሱ፡፡
በሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል፡፡
በዚህ ወቅት ሚኒስትሩ በመጪው ሃገራዊ ምርጫ፣ በታላቁ የህዳሴ ግድብ፣ በትግራይ ክልል እየተደረገ ስላለው ሰብአዊ ድጋፍና የመልሶ ማቋቋም እንዲሁም በኢትዮ ሱዳን የድንብር ውዝግብ ጉዳይ ለፕሬዚዳንቱ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በበኩላቸው የናይል ተፋሰስ ሃገራት ከወንዙ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ባሉ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር በስብሰባ መልክ ጉባኤ ጠርተው እንዲወያዩ ሃሳብ አቅርበዋል፡፡
በሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ ባለፈው ሳምንት ለደቡብ ሱዳን እና ሩዋንዳ መሪዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተላከ ደብዳቤን ማድረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ምንጭ፡- ኤፍ ቢ ሲ ፤ሰኔ 4 ፣ 2013

嵌套Portlet

资源发布器