ሱዳን ከግድቡ ጋር ተያይዞ ላሉ ልዩነቶች የአፍሪካ ህብረት መፍትሄ እንደሚሰጥ እምነቷ መሆኑን ገለፀች - መነሻ - am

嵌套Portlet

资源发布器

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ 星期五, 17 六月 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች 星期三, 8 六月 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ 星期三, 8 六月 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

资源发布器

ሱዳን ከግድቡ ጋር ተያይዞ ላሉ ልዩነቶች የአፍሪካ ህብረት መፍትሄ እንደሚሰጥ እምነቷ መሆኑን ገለፀች
በኢትዮጵያ ከታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ ያሉ ልዩነቶች በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ይፈታሉ የሚል ጠንካራ እምነት እንዳላት ሱዳን ገለፀች።
በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ውጤታማ እና ፈጣን መፍትሄ ላይ እንደሚደረስ እምነቷ መሆኑንን አስታውቃለች።
ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ በሚለው መሪ ቃል የሶስትዮሽ ድርድሩ እንዲቀጥል ፍላጎት እንዳላትም ነው ሱዳን የገለፀችው።
የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ወሳኙን እና አዲስ ሃሳብና አሰራር የሚመጣበትን የአፍሪካ ህብረትን እንደሚያደንቅ መግለፁን ሱና ዘግቧል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም ሱዳን አቋሟን ለማስረዳት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ የሚመራ ልዑክ ወደ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ ኬንያ ፣ ሩዋንዳ እና ኡጋንዳ እንደምትልክ ገልጻለች።
ኤፍ ቢ ሲ

嵌套Portlet

资源发布器