ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ - መነሻ - am
嵌套Portlet
资源发布器
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
网页内容搜索
资源发布器
ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡
የአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ የአዳማ ከተማ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት፣አባ ገዳዎች፣ ሃደ ስንቄዎች እንዲሁም የተለያዩ የማኀበረሰቡ ክፍሎች በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል።
በመክፈቻ መርሃ-ግብሩ ላይ የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኃይሉ ጀልዴ፥ ግድቡ የሀገራችን ሉዓላዊነትና የአንድነታችን ምልክት ነው ያሉ ሲሆን ግድቡ በዜጎች ተሳትፎ እንደተጀመረው ሁሉ በዜጎች ጉልበት፣ ሐብት እና አቅም በመጨረስ ለዓለም ተምሳሌት እንሆናለን ብለዋል።
የአዳማ ከተማ ነዋሪዎችና ባለሐብቶችም በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን በግንባር ቀደምትነት በመሳተፍ ያሳዩትን ላቅ ያለ ተሳትፎ ለግድቡ መሳካትም በማበርከት የድርሻቸውን እንዲወጡ መልዕክት ማስተላለፋቸውንም ከከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ምንጭ፡- ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት
嵌套Portlet
资源发布器
— 每页项目