አ/አደሩ በገጠራማ አካባቢዎች በአፈርና ውሀ ጥበቃ ረገድ የሚያደርገው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ እውቅና ሊሰጠው እንደሚገባ ውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ አስታወቁ ፡፡ - መነሻ - am

嵌套Portlet

资源发布器

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ 星期五, 17 六月 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች 星期三, 8 六月 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ 星期三, 8 六月 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

资源发布器

አ/አደሩ በገጠራማ አካባቢዎች በአፈርና ውሀ ጥበቃ ረገድ የሚያደርገው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ እውቅና ሊሰጠው እንደሚገባ ውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ አስታወቁ ፡፡

ሚኒስትሩ ዛሬ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ም/ቤት ጽ/ቤት በግዮን ሆቴል ባዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ተፈጥሮን ባለበት ለማቆየት ብሎም የተራቆቱ አካባቢዎችን እንዲያገግሙ ለማድረግ አርሶአደሩ እያደረገ ያለው ጥረት ከፍተኛ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የአባይ ተፋሰስን ጨምሮ በሁሉም ተፋሰሶች 6ቢሊዮን ችግኞች ለመትከል በዕቅድ ተይዞ ከግንቦት ወር መጨረሻ ጀምሮ ችግኝ ተከላ ሲካሄድ መቆየቱንና እስካሁን የዕቅዱን 75 በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል፡፡ለዓለም ተምሳሌት መሆን የሚያስችል ሥራ እየተሰራ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ችግኝ ከመትከል ባለፈ እንዲጸድቁ አስፈላጊው እንክብካቤ ሊደረግ ይገባል ብለዋል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ም/ቤት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሔ በበኩላቸው የህዳሴ ግድብን በራሳችን አቅም ከሰራን ማደግና ከጥገኝነት መላቀቅ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡ የህዳሴ ግድብ ትስስር በሰኔ ወር አጋማሽ መመስረቱን ያስታወሱት ዶ/ር አረጋዊ ትስስሩ በሀብት አሰባሰብ ፣በፐብሊክ ዲፕሎማሲ፣በአካባቢ ጥበቃና በሚዲያ ሥራዎች ላይ አተኩሮ የሚሰራ መሆኑን ገልጸው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ትስስሩን ተጠቅሞ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የሀብት አሰባሰብ፣የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ፣የአካባቢ ጥበቃ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች የህዳሴ ግድብ ትስስር በቀጣይ በሚያከናውናቸው ተግባራት ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

嵌套Portlet

资源发布器