የየህዳሴው ግድብ ተጠናቆ ሪቫን እስከሚቆረጥ ድጋፋቸን ተጠናክሮ ይቀጥላል - የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ - መነሻ - am

嵌套Portlet

资源发布器

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ 星期五, 17 六月 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች 星期三, 8 六月 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ 星期三, 8 六月 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

资源发布器

የየህዳሴው ግድብ ተጠናቆ ሪቫን እስከሚቆረጥ ድጋፋቸን ተጠናክሮ ይቀጥላል - የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ

የየህዳሴው ግድብ ተጠናቆ ሪቫን እስከሚቆረጥ ድጋፋቸን ተጠናክሮ ይቀጥላል - የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ ) የህዳሴው ግድብ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ሪቫን እስከሚቆረጥ ድረስ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ገለፁ።

በዩንቨርስቲው የሁለተኛ ዙር የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትን አስመልክቶም ደስታቸውን እና ድጋፋቸውን ለአንድ ደቂቃ በማጨብጨብ ገለፀዋል።

የግድቡ የሁለተኛ ዙር ሙሌት ታሪካዊ ነው ያሉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ሙሌቱም የተጠናቀቀው በሀገራችን ላይ የውጭ ሀገራት ከፍተኛ የሆነ ጫናና በሀገር ውስጥም እንዲሁ ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ ችግር ውስጥ ባለንበት ወቅት መሆኑ ታሪካዊ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

ግድቡ በኢትዮጵያዊያን ዜጎች እና በትውልደ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ ብቻ የሚሠራ በመሆኑ ታሪካዊነቱን ያጎላዋል ያሉት ፕሬዝዳንቱ በህዝባችንና በህዝባችን ብቻ ዛሬ ለደረሰበት ለሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት የደረሰ በመሆኑ በቀጣይ የአባይ ግድብ ሪቫን እስከሚቆረጥ ድረስ ሁሉምእጅ ለእጅ ተያይዞ መስራት እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል የግቢው ማህበረሰብም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል ።

የሁለተኛውን ዙር ሙሌት ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው በዚሁ መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲው ም/ኘሬዝዳንቶች÷ ዳይሬክተሮች÷ የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ሠራተኞች÷ መምህራን እና ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን ደሰታቸውንና ምስጋናቸውን ለአንድ ደቂቃ ያክል በማጨብጨብ ገልፀዋል::

በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የዩኒቨርስቲው የማህበረሰብ አባላትም 8100A ላይ ድጋፋቸውን በመላክ የወትሮ አጋርነታቸውን አሳይተዋል።

fbc

嵌套Portlet

资源发布器