የህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር የሚታየው በጸጥታው ምክር ቤት ሳይሆን በአፍሪካ ህብረት ነው-ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን - መነሻ - am

嵌套Portlet

资源发布器

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ 星期五, 17 六月 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች 星期三, 8 六月 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ 星期三, 8 六月 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

资源发布器

የህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር የሚታየው በጸጥታው ምክር ቤት ሳይሆን በአፍሪካ ህብረት ነው-ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን

የህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር የሚታየው በጸጥታው ምክር ቤት ሳይሆን በአፍሪካ ህብረት መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚስትር ደመቀ መኮንን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የተፋሰሱ ሀገራት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱም ታላቁ የህዳሴ ግድብ የታችኞቹን የተፋሰሱ ሀገራት በማይጎዳ መልኩ በፍትሀዊነት እና በምክንያታዊነት የሚጠቅም የጋራ ፕሮጀክት መሆኑን አቶ ደመቀ አብራርተዋል፡፡

ሱዳን እና ግብጽ በማይገባ መልኩ የህዳሴውን ግድብ ወደ ጸጥታው ምክር ቤት እና የዓረብ ሊግ አባል ሀገራት በመውሰድ አለም አቀፋዊ እና የደህንነት ጉዳይ አደርገውታልም ነው ያሉት፡፡

ሁለቱ ሀገራት የአፍሪካ ህብረትን ሚና ዝቅ በማድረግ የጀመሩትን እንቅስቃሴ በመተው ጉዳዩን ወደ አፍሪካ ህብረት እንዲያመጡት እና የቅኝ ግዛት ዘመን አካሄድን እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የውይይት መድረኩ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር የደረሰበትን ሁኔታ በተመለከተ ለሀገራቱ ማብራሪያ ለመስጠት ያለመ ነው፡፡

ኤፍ ሰኔ 30 2013

嵌套Portlet

资源发布器