Asset Publisher

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የ2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የ2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ
በአሜሪካ የሳክራሚንቶ እና አካባቢው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት የ2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡
የማህበረሰቡ ተወካዮች ድጋፉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ሲያስረክቡ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ደግሞ ለማህበሩ የምስጋና የምስክር ወረቀት አበርክተዋል፡፡
በርክክብ ሥነስርዓቱ ላይ ሥራ አስኪያጁ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ እንደገለፁት የኢትዮጵያ አጋሮችና ኮንትራክተሮች ሳይቀሩ ግድቡን እንዳይሰሩ ጫና እየተረገ ባለበት ጊዜም መላው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለፕሮጀክቱ ግንባታ ያደረጉት ድጋፍ የሚያስደንቅ ነው ብለዋል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አንደኛው ዩኒት ኃይል ማመንጨት የጀመረ ሲሆን ሁለተኛውን ዩኒት ወደ ሥራ ለማስገባት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ሙሉ ወጭ እየተገነባ የሚገኘው ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ለፍሬ ይበቃል ያሉት ኢንጅነር ክፍሌ ለዚህም የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የማህበሩ ተወካይ አቶ አስማማው ኑሬ በበኩላቸው ከኢትዮጵያ ውጭ የሚኖረው አትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የፕሮጀክቱን ግንባታ በቅርበት እየተከታተለ ሲሆን ድጋፉም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነት አለኝ ብለዋል፡፡
ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል