Asset Publisher

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ለኅዳሴ ግድብ 42 ሚሊየን ብር ተሰበሰበ
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ለታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ 42 ሚሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ።
የታላቁ ኅዳሴ ግድብ ዋንጫ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን የነበረውን ቆይታ አጠናቆ ወደ ምዕራብ ሀረርጌ ዞን ተሸኝቷል።
በሽኝት መርኃ ግብሩ ዋንጫው በዞኑ በነበረው ቆይታ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆን አስተዋጽኦ ላበረከቱና በቦንድ ግዢ የላቀ ተሳትፎ ላደረጉ አካላት የእውቅና መርኃ ግብር በአወዳይ ከተማ ተካሂዷል።
ዋንጫው በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በነበረው የአንድ ሳምንት ቆይታ 42 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን የዞኑ አስተዳዳሪ ሚስኪ መሀመድ ገልፀዋል።
በዚህም ባለሃብቱን፣ አርሶ አደሩ እና በየደረጃው የሚገኘው የኅብረተሰቡ ክፍልን በማነቃነቅ በተከናወነ ሥራ ዋንጫው በዞኑ በነበረው የአጭር ጊዜ ቆይታ ከታቀደው እቅድ በላይ ማሳካት እንደተቻለ ተናግረዋል።
በምዕራብ ሀረርጌ በሚኖረው የአንድ ሳምንት ቆይታም 19 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱ ተገልጿል።
በሽኝት መርኃ ግብሩ የምስራቅና የምዕራብ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ የሚመለከታቸው አካላትና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
ዋልታግንቦት 15/ 2014