Asset Publisher

የግድቡ ስራ አስኪያጅ ማስተባበያ እና የግብጽ ሚዲያዎች

የግድቡ ስራ አስኪያጅ ማስተባበያ እና የግብጽ ሚዲያዎች

በግብጽ ሚዲያ ዘንድ ኢትዮጵያ የምታስገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ በግብጽ እና በሱዳን ድርቅ ቢከሰት ውሃ አትለቅም ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ የግድቡ ስራ አስኪያጅ አስተባበሉ።

እንደዚህ አይነት ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እና ፍላጎት በመሪዎች እና በፕሮጀክቱ መሪዎች ይቅርና ማንም ኢትዮጵያዊ የለውም ያሉት የታላቁ ህዳሴው ግድብ ስራ አስኪያጅ ክፍሌ ሆሮ (ኢንጂነር) ስማቸው መጠቀሱ እና አስተያየት ሰጥተዋል መባሉ ከእውነት የራቀ መሆንኑን ለአሐዱ ተናግረዋል።

ሙሌቱም ይሁን የህዳሴው ግድብ የሚሰራበት መንገድ የላይኛው ተፋሰስ አገራት ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ እና የጋራ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ ይከናወናል ባይ ናቸው።

የህዳሴው ግድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታገል ቀኑብህ በበኩላቸው መሰል ወሬዎችን የውሸት ፈጠራዎች ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል። ምናልባትም የዚህ አይነት የውሸት መረጃ ዓላማው በግብጽ እና በሱዳን የውስጥ የቤት ስራ ሲበዛ የትኩረት አቅጣጫዎችን ለማስቀየር የሚጠቀሙባቸው መንገዶች ናቸው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከተፋሰሱ አገራት ጋር ለምክክር በሯ ክፍት መሆኑን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ለሶስተኛውን ዙር የውሃ ሙሌት ለማካሄድ ምንጥጣሮ ተጀምሯል። በእቅዱ መሰረትም ሃምሌ ወር ውስጥ ሙሌቱ ይከናወናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አስታውሰዋል።

መረጃ ለመገናኛ ብዙሃንም ይሁን ለሰፊው ህዝብ ይፋዊ በሆነ መንገድ የሚሰጠው ትልልቅ ክስተቶች በግድቡ ዙሪያ ሲኖሩ ነው፤ ዜጋውም መረጃዎች ከየት እንደመጡ ማጣራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

አሐዱ ቴሌቭዥን