የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ያለፉት 6 ወራት የስራ አፈጻጸሙን ገመገመ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ያለፉት 6 ወራት የስራ አፈጻጸሙን ገመገመ

የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ያለፉት 6 ወራት የስራ አፈጻጸሙን ገመገመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የ2013 በጀት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ተካሂዷል።

የታላቁ የኢትዮጲያ የህዳሴ ግድብ የህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት በጅግጅጋ ከተማ ባካሄደው የግምገማ መድረክ ላይ የማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄን፣ የሶማሌ ክልልን ጨምሮ ከሁሉም ክልሎች፣ ከአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የግምገማ መድረኩ በ2013 የበጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት በዋናው ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱና በየክልሎች የሚገኙ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቶች የተከናወኑ ስራዎችን ለመገምገምና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው ተብሏል።

በመድረኩ ላይ የግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ስራዎች የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በአፈፃፀሙ ላይ የታዩ ክፍተቶችን በማሻሻል ጠንካራ ጎኖችን በማጠናከር በቀጣይ ሊሰሩ በሚገቡ ስራዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት መካሄዱን ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙኀን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.