ለህዳሴ ግድቡ በ48 ሰዓታት ከዳያስፖራው 70 ሺህ ዶላር ተሰበሰበ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ለህዳሴ ግድቡ በ48 ሰዓታት ከዳያስፖራው 70 ሺህ ዶላር ተሰበሰበ
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ የሚደረግበት ድረ ገፅ ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ከ583 ዳያስፓራዎች 70 ሺህ 380 ዶላር መሰብሰቡ ተገለፀ፡፡
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጰያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች www.mygerd.com የሚል ድረ ገጽ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በ48 ሰዓታት ውስጥ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ 70 ሺህ 380 ዶላር ድጋፍ መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡
በተቋሙ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት÷ድረ ገፁ በተከፈተ 48 ሰዓታት ውስጥ 583 ለጋሾች ለህዳሴ ግድቡ 70 ሺህ 380 ዶላር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ÷ድረ ገጹ የፈለጉትን መጠን ማስገባት እንዲችሉ ክፍት የሆነ ሲሆን 36 ሰዎች ግድቡን በተለያየ መንገድ እንደግፍ የሚል ዘመቻ እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡
የተሰበሰበው በአማካኝ በሰአት ሲታይ 1 ሺህ 510 ዶላር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ይህ ደግሞ ዲያስፖራው በቁጭት እየደገፈ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡
ኤፍ ቢ ሲ፣ ሐምሌ 19 ፣ 2013

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.