የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ20 ሚሊዮን ብር የሕዳሴ ግድብ ቦንድ ገዛየፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ20 ሚሊዮን ብር የሕዳሴ ግድብ ቦንድ ገዛ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ20 ሚሊዮን ብር የሕዳሴ ግድብ ቦንድ ገዛየፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ20 ሚሊዮን ብር የሕዳሴ ግድብ ቦንድ ገዛ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ20 ሚሊዮን ብር የሕዳሴ ግድብ ቦንድ ገዛ
ለግድቡ በአምስት ወራት ከ888 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን ለማገዝ የ20 ሚሊዮን ብር የቦንድ ግዥ ፈፀመ።
የቦንድ ግዢው የግድቡን ግንባታ ለማጠናቀቅ የኅብረተሰቡ ተሳትፎ እንዲያድግ መንግሥት ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ የተደረገ መሆኑን ትናንት በተደረገው የርክክብ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገልጿል። የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽንን በመወከል ቼኩን ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት ያስረከቡት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ረሻድ ከማል ናቸው።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት፤ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለተለያዩ ሀገራዊ ልማት ፕሮጀክቶች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታውሰው፤ ለኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚያደርገውን ድጋፍ በልዩ ሁኔታ በመመልከት ሰፊ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህንንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ህዝብ ሀብት የሆነው የህዳሴው ግድብ እስኪጠናቀቅ ድረስ ኮርፖሬሽኑ ታሪካዊ አሻራውን ማኖሩን አበክሮ ይቀጥላል።
ኮርፖሬሽኑ ከዚህ ቀደም ባደረጋቸው የገንዘብ አስተዋጽኦዎች ለገበታ-ለሀገር ፕሮጀክት 20ሚሊዮን ብር፣ ለመቄዶኒያ የአረጋዊያን መኖሪያ ግንባታ 5 ሚሊዮን ብር፣ የ COVID-19 ስርጭትን ለመከላከል እየተደረገ ላለው ሀገራዊ ርብርብ 10 ሚሊዮን ብር፣ ባለፉት 6 ወራት የኮርፖሬሽኑ ተከራይ ደንበኞች 50% የቤት ኪራይ ክፍያ እንዲቀነስላቸው በማድረግ 400 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የተደረገ ሲሆን፤ ለገበታ-ለሃገር የተሰጠውን 20 ሚሊዮን ብር ጨምሮ በድምሩ 455 ሚለዮን ብር ገደማ ወጪ በማድረግ ኮርፖሬሽኑ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ እንደሚገኝም አቶ ረሻድ ጠቁመዋል።
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አረጋዊ በርሔ በበኩላቸው፤ የሕዳሴ ግድብ ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ለውጥ ወሳኝ ነው ብለዋል። ኮርፖሬሽኑ ያደረገው ድጋፍ ለሌሎች ተቋማት አርአያ የሚሆን ተግባር እንደሆነ የጠቆሙት ዶክተር አረጋዊ፤ ሁሉም ተቋማትና ዜጎች ተሳትፎአቸውን በማሳደግ ግድቡን ለማጠናቀቅ የሚደረገውን ርብርብ እንዲደግፉም ጥሪ አቅርበዋል።
ባለፉት አምስት ወራት ብቻ መላ ኢትዮጵያውያን በአገር ውስጥና በውጪ ከ790 ሚሊዮን ብር በላይ የቦንድ ግዥ ድጋፍ ማደረጋቸውንና በ8100 የገቢ ማስገኛ ፕሮግራምም ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የግድቡ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍቅርተ ታምር ገልጸው፤ ይህም በግድቡ ግንባታ ታሪክ ከፍተኛ አስተዋጽኦ መሆኑን አስታውቀዋል።

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.