የህዳሴ ግድብ 2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት እየተከናወነ ያለው ሶስቱ አገራት በፈረሙት የመርህ ስምምነት መሰረት ነው – ኢ/ር ጌዲዮን - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የህዳሴ ግድብ 2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት እየተከናወነ ያለው ሶስቱ አገራት በፈረሙት የመርህ ስምምነት መሰረት ነው – ኢ/ር ጌዲዮን

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት እየተከናወነ ያለው ሶስቱ አገራት በፈረሙት የመርህ ስምምነት መሰረት መሆኑን የግድቡ ተደራዳሪና የባለሙያዎች ቡድን ሰብሳቢ ኢንጅነር ጌዲዮን አስፋው ገለጹ።

ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን እኤአ 2015 በመሪዎቻቸው አማካኝነት በሱዳን ካርቱም የህዳሴ ግድብ ድርድርን አስመልክቶ የመርሆዎች ስምምነት መፈረማቸው ይታወሳል።

የመርህ ስምምነቱ አስር አንቀጾችን ያካተተ ሲሆን የሶስቱንም አገራት ፍትሃዊና ምክንያታዊ የውሃ አጠቃቀም ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ይታወቃል።

ሁለተኛው ዙር የግድቡ የውሃ ሙሌት በዚሁ ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን በፈረሙት የመርህ ስምምነት መሰረት እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጰያ ህዳሴ ግድብ ተደራዳሪና የባለሙያዎች ቡድን ሰብሳቢ ኢንጅነር ጌዲዮን አስፋው ገልጸዋል።

በግድቡ የውሃ ሙሌት ዙሪያ የሶስቱም አገራት ባለሙያዎች አስቀድመው የተስማሙባቸው ነጥቦችም በዚሁ የመርህ ስምምነት መካተታቸውን ኢንጅነር ጌዲዮን አስታውሰዋል።

የመርሆዎች ስምምነቱ አገራቱ ስምምነቱን በተፈራረሙ 15 ወራት ውስጥ ሁለት ጥናቶች እንዲካሄዱ ቢደነግግም ግብጽና ሱዳን ጥናቱ እንዳይካሄድ በያዙት ግትር አቋም ሳይሳካ ቀርቷል ብለዋል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግብጽና ሱዳን የግድቡን የውሃ ሙሌት በተመለከተ የሚሰጡትን የተዛባ መረጃ ሊመረምር እንደሚገባም ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የግድቡን የውሃ ሙሌት የተመለከቱት የመርህ ስምምነቱ አንቀጾች በግብፅና ሱዳን የውሃ ባለሙያዎች የሚታወቁና ከመግባባት ላይ የተደረሰባቸው መሆናቸውንም አንስተዋል።

ኤፍ ሰኔ 30 2013

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.