ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል -ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ሐምሌ 12 ቀን 2013 ዓ.ም የሁለተኛውን አመት የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፈሰስ መጀመሩን የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል -ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ሐምሌ 12 ቀን 2013 ዓ.ም የሁለተኛውን አመት የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፈሰስ መጀመሩን የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ በትዊተር ገጻቸው ላይ ÷ ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል ብለዋል።
ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችም እንኩዋን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ይህ ውጤት ማለት ሁለት ተርባይኖችን ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልገውን የውሀ መጠን ይዘናል ማለት ነው ሲሉም ገልጸዋል።
በዘንድሮው አመት በአባይ ተፋሰስ እየዘነበ ያለው ውሃ መጠን ከፍተኛ ሲሆን÷ ይህም ከፈጣሪ የተሰጠን ፀጋ ምን ያህል ትልቅ እንደሆነና እንዴት እያገዘን እንደሆነ መረዳት እንችላለን ለዚሁም ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል ሚኒስትሩ።
እዚህ ደረጃ ለመድረስ በዘንድሮው አመት መጠነ ሰፊ ስራ ሰርተናል÷ በቀጣይ ሁለቱ ተርባይኖች እንዲያመነጩ ብርቱ ስራዎች እየተሰሩ ነው እናም ያንን በቅርብ ወራት በማጠናቀቅ የልፋታችን ሌላው ዋነኛ ውጤት ላይ እናደርሳለን ብለዋል።
ምንጭ፡- ኤፍቢሲ

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.