በካናዳ ማኒቶባ ግዛት ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ106 ሺህ የካናዳ ዶላር በላይ ተሰበሰበ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

በካናዳ ማኒቶባ ግዛት ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ106 ሺህ የካናዳ ዶላር በላይ ተሰበሰበ

በካናዳ ማኒቶባ ግዛት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ 106 ሺህ የካናዳ ዶላር በላይ መሰብሰቡን በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።

በካናዳ የተቋቋመው የጥምረት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የማኒቶባ ቻፕተር በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በማኒቶባ ግዛት በዊኒፔግ ከተማ እና ብራንደን ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያንን በማቀናጀት ባዘጋጁት የቨርቹዋል ኮንፈረንስ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም 44 ሺህ 575 የካናዳ ዶላር ነፃ ድጋፍ የተደረገ፣ 13 ሺህ 550 ነፃ ድጋፍ ለማድረግ ቃል የተገባ ሲሆን፣ በተጨማሪም 47 ሺህ 900 የካናዳ ዶላር የቦንድ ግዢ በቀጥታ ከሀገር ቤት ለመፈፀም ቃል የተገባ መሆኑ ተገልጿል።

ፕሮግራሙ በተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያውያን በዚህ ወሳኝ ጊዜ በፅናት አብረው በመቆም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ሙሌት እንዲሳካ ድጋፋቸውን አጠናክረው መቀጠል አንደሚገባቸው አሳስበዋል።

በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በካናዳ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙ ላይ ካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ እያደረጉ የሚገኙት ተከታታይ የገቢ ማሰባሰቢያ እንቅስቃሴ የሚያኮራ መሆኑን ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ የተለያዩ ግዛቶች ውስጥ ከሚገኙ የጥምረት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቻፕተሮች ጋር በመተባበር አስካሁን በተካሄዱ 15 መድረኮች በስጦታ ብቻ 376 ሺህ የካናዳ ዶላር በላይ መሰብሰብ መቻሉንም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ካለችበት ውስብብ ሁኔታ እና የረሷን ተፈጥሮ ሀብት ተጠቅማ ዜጎቿን ከድህነት ለማላቀቅ የምታደርገውን ጥረት ለማሰናከል ከውስጥ እና ከውጭ ከተጋረጠባት ጫና አንፃር ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሀገሩ ጉዳይ ላይ አርበኛ በመሆን የሚያደርገውን ዘርፈብዙ ድጋፎች አጠናክሮ እንዲቀጥልም አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ጥሪ አቅርበዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት ተሳታፊዎች በነፃ ድጋፍ እና በቦንድ ግዥ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል መግባታቸውን በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገልጿል።

ምንጭ፡- ኢቢሲ፤ ሰኔ 18/2013

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.