ግድቡን ከደለል ለመታደግ ህብረተሰቡ 100 ቢሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ግድቡን ከደለል ለመታደግ ህብረተሰቡ 100 ቢሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ

ግድቡን ከደለል ለመታደግ ህብረተሰቡ 100 ቢሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከደለል ለመታደግ ህብረተሰቡ በአፈር እና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች ላይ በመሳተፍ 100 ቢሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ ማድረጉን ሀገር አቀፉ የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ገለጸ።
"አንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት፤ ለተቀናጀ የአባይ ተፋሰስ ልማት" በሚል መሪ ሀሳብ ትናንት በአሶሳ ከተማ የተጀመረው አራተኛው ሃገር አቀፍ ተፋሰስ ልማት የተሞክሮ ልውውጥ የምክክር መድረክ ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡
ሀገር አቀፉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አባል ኢንጂነር ጌታሁን ሁሴን በወቅቱ እንዳሉት ጽህፈት ቤቱ በተለይ በአባይ ወንዝ ተፋሰስ የሚገኝበት ክልሎችን የተፋሰስ ልማት በቅንጅት እንዲሠሩ እያደረገ ነው፡፡
እስካሁን አርሶ አደሩ እና አርብቶ አደሩ ጨምሮ ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል ተፋሳሰን መሰረት ባደረገ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች ላይ በመሳተፍ 100 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
ይህም የህዳሴውን ግድብ ከደለል መታደግ ብቻ ሳይሆን ለሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ግባችን ስኬት ሚናው የጎላ ነው ብለዋል፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃ እና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ታደሰ በበኩላቸው በሃገሪቱ በየዓመቱ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና ልማት የማይከናወንበት ክልል እንደሌለ ተናግረዋል፡፡
በዚህም ህብረተሰቡ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቁመው ይሁንና በአፈርና ውሃ ጥበቃ የለማውን አካባቢ በባለቤትነት የሚመራው አካል አልተዋቀረም ብለዋል።
ሚኒስቴሩ ልማቱ ቀጣይነቱ አስተማማኝ እንዲኖረው የአካባቢ ጥበቃና ልማት ሥራውን በባለቤትነት የሚመራ ተቋም ለማመቻቸት እንቀስቃሴ መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡
በሃገሪቱ የተፋሰስ ልማት መጠናከር የህዳሴውን ግድብ ህልውና እንደሚያስጠብቅ የተናገሩት ደግሞ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተወካይ አቶ ባበክር ከሊፋ ናቸው።
የመሬት ለምነት በማሳደግ እና የሥራ ዕድል አማራጮችን በማስፋት ስደትን ያስቀራል ብለዋል።
ከኦሮሚያ ክልል የመጡት አርሶ አደር ሼህ አብደላ ሳኒ በሰጡት አስተያየት በአካባቢያቸው 20 ሄክታር የተራቆተ መሬት ማልማት እንደቻሉ በማውሳት ተሞክሯቸውን አካፍለዋል፡፡
በጋራ ካልሠራን የወደመውን የተፈጥሮ ሃብታችን በአጭር ጊዜ መመለስ አዳጋች ነው፤ ከፌደራል እና ክልሎች ብሎም የሚመከታቸው አካላት ተቀናጅተን እንስራ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በግላቸው የተፈጥሮ ሃብት ሥራውን ለመቀጠል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ከአማራ ክልል የመጡት አርሶ አደር አባይነህ ብርሃኑ በበኩላቸው በምክክር መድረኩ በአካባቢያቸው ከተከናወኑ ተፋሰስ ልማት የተለየ ተሞክሮ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
ከግብርና ባለሙያዎች እና ሌሎች አርሶ አደሮች በመቀናጀት ያገኙትን ተሞክሮ ተጠቅመው የተጠናከረ የአፈርና ወሃ ጥበቃ ሥራ እንደሚያከናውኑ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በምክክር መድረኩ ከፌደራልና ሁሉም ክልሎች የተወጣጡ ከ60 በላይ ተወካዮች እየተሳተፉ ሲሆን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚገኙ የአባይ ገባር ከሆነው ዳቡስ ወንዝ ዳር የተከናወኑ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች እንደሚገበኙም ይጠበቃል።

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.