ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 10,000 ብር በስጦታ ተበረከተ - መነሻ - am
Nested Portlets
Asset Publisher
Statistics
Web Content Search
Asset Publisher
በውሃና ኢነርጂ ኤግዚቢሺን ላይ ሲታደሙ ያገኘናቸው አቶ ጌታቸው መንገሻ ለግድቡ ግንባታ የሚውል 10,000 ብር በስጦታ አበርክተዋል፡፡
አቶ ጌታቸው መንገሻ ነዋሪነታቸው በዩናይትድስቴት ኦፍአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት ሲሆን ውጭ ሀገር መኖር ከጀመሩ ከ20 ዓመታት በላይ ሆናቸዋል፡፡
ታዲያ ቤተዘመድ ለመጠየቅ ወደ ሀገር ቤት በቅርቡ እንደመጡ የሚናገሩት አቶ ጌታቸው መንገሻ የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ኤግዚቢሺን በብሄራዊ ሳይንስ ሙዚየም ለእይታ ክፍት እንደሚሆን ሲሰሙ እጅግ መደሰታቸውን ገልጸዉልናል፡፡
አቶ ጌታቸው መንገሻ ሁሌም ስለሀገራቸው የሚያስቡ ከመሆናቸውም በለይ የህዳሴ ግድብ ተገንብቶ የሚጠናቀቅበት ጊዜ እንደናፈቃቸውና በጉግት እንደሚጠብቁት ተናግረው በግላቸው ማድረግ ሚገባቸውን ሁሉ ለማድረግ እንደሚሞክሩ ገልጸዋል፡፡
አምና ወደ ሀገር ቤት በመጡ ሰዓትም 10,000 ብር ለግድቡ ግንባታ የለገሱ ከመሆኑም በላይ ለመከላከያ ሰራዊት እንዲሁም በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ለተፈናቀሉ ዜጎች የበኩላቸውን ድርሻ ማበርከታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ታላቁ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ከፍ ወዳለ ማማ የሚያደርስ ግድብ በመሆኑ ሌሎችም እንደዚሁ የየአቅማቸውን እየረዱ ሀገራችን በህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲሁም በሌሎች የልማት ዘርፎም ውጤታማ እንድትሆን መተባበር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በአጠቃላይ በዘርፉ የተሰሩ ስራዎች እጅግ ተስፋ ሰጪና ኤግዚቢሺኑም ሳቢ በሆነ መልኩ የተሰዳ በመሆኑ ባዩት ነገር ስለመድሰታቸው ገለጽው የህዳሴ ግድብን እቦታው ድረስ ሄደው የመጎብኘት ዕቅድ እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡