የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ የተጣለበት 10ኛ ዓመት - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ የተጣለበት 10ኛ ዓመት
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ የተጣለበት 10ኛ ዓመት
ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የቀረበ መልዕክት፡-
መላው ኢትዮጵያውያን፣ በትውልድ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጅ ህዝቦችና ሀገራት በሙሉ፡ የአንድነታችን እና የሉዓላዊነታችን አርማ የሆነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ ለተጣለበት 10ኛ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ! አደረሰን!
ባለፉት አሥር ዓመታት ኢትዮጵያውያን ታላቁ የህዳሴ ግድባችንን ለመገንባት አንድ ሆነን ተረባርበናል፡፡ በግድቡ ግንባታ ሂደትና በሶስትዮሽ ድርድሩ ያጋጠሙንን አያሌ ፈተናዎችን በማለፍ ዛሬ ላይ ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ በቦንድ ግዢ፣ በልገሳ እና በሌሎች ገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶች ድጋፍ አድርገናል፤ ግድባችንንም ከ79 በመቶ በላይ አድርሰናል፣ የመጀመሪያ ዙር የውሀ ሙሌትም በስኬት ተከናውኗል፡፡ የውሃ ሙሌቱን ተከትሎም የህዝቡ ድጋፍ በመጨመሩ ከሀምሌ 2012 እስካሁን ድረስ በ9 ወራት ብቻ 1 ቢሊዮን 484 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተሰብስቧል፡፡
ዘንድሮ ለ2ኛ ዙር የውሃ ሙሌት እና የመጀመሪያ የሙከራ ምርት ለማከናወን የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡ ህዝባችን ለግድቡ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ድጋፍ ከማድረግ ጎን ለጎን የዲፕሎማሲያዊ ሂደቱን በንቃት በመከታተል ከፍተኛ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና የሚዲያ ዲፕሎማሲ ስራ በመስራት ሀገራችን ውጣ ውረዶችን በአሸናፊነት እንድትወጣ የበኩሉን ሚና እየተወጣ ይገኛል፡፡
የሶስትዮሽ ድርድሩን ሂደት እና የመጀመሪያውን ዙር የውሀ ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ ተከትሎ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያሳየውን መነቃቃትና ሲያደርግ የቆየውን ሁለንተናዊ ድጋፍ ወደፊት አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ግድቡን ከደለል ስጋት ለመታደግ የሚያስችሉ በአባይ ተፋሰስና በሌሎችም አካባቢዎች ሲካሄዱ የቆዩ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራዎችም ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው፡፡
ባጠቃላይ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ማጠናቀቅ ለኢትዮጵያውያን አንድነት ህልውናና ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጉዳይና ብሎም ከድህነትና ጉስቁልና ወደ እድገትና እርካታ አሻጋሪ መሆኑን ለአፍታም ቢሆን ሳንዘነጋ ለግድቡ ግንባታ የጀመርነውን ድጋፍ እስከ ፍጻሜው አጠናክረን እንድንቀጥል የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎው ማስተባበርያ ጽ/ቤታችን የዘወትር ጥሪውን ያቀርባል፡፡ እስካሁን መላው ህዝባችን፣ መንግስታችን እና ሌሎች በጎ-አሳቢ አካላትም ለግድቡ ግንባታ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
ኢትዮጵያውያን ዕርስ በርስ በመረዳዳት ራሳችንን ከኮቪድ 19 እየጠበቅን፤ ሰላማችንን እያረጋገጥን ፣ ግድባችንን በጋራ እንድናጠናቅቅ ጽ/ቤታችን አደራ ይላል፡፡
‹‹ጤናችን ይጠበቃል! ግድባችን ይጠናቀቃል!››
‹‹ግድባችን ለአንድነታችን እና ሉዓላዊነታችን! ››
በድጋሚ መልካም 10ኛ ዓመት! እናመሰግናለን !

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.