ዲያስፖራው ለህዳሴና ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ከ1ነጥብ5 ሚሊዮን ዶላር በላይ አበረከተ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ዲያስፖራው ለህዳሴና ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ከ1ነጥብ5 ሚሊዮን ዶላር በላይ አበረከተ


አዲስ አበባ:- በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴው ግድብ እና ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች የሚውል ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዶላር በላይ መስጠታቸውን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ ዳያስፖራው በሦስት ወራት ውስጥ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል ከአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ዶላር በላይ በጥሬ ገንዘብ እና ቃል የተገባ ገንዘብ ተለግሷል። ከዚህ ውስጥ ከ750 ሺህ ዶላር በላይ በቀጥታ በጥሬ ገንዘብ ገቢ የተደረገ ነው። ይህም የዳያስፖራውን ለህዳሴ ግድብ የሚያደርገው ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉን ያሳያል።
እንደ ወይዘሮ ሰላማዊት፤ የኮቪድ በሽታ በዓለም ሃገራት በተለይም በአደጉት ሀገራት በርትቶ ባለበት ሁኔታ ዳያስፖራው የስራ እና የገቢ ችግር ሊያጋጥመው እንደሚችል ይታወቃል። ይሁንና የሀገር ጉዳይ ይቀድማል በሚል ከ1ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ አድርጓል።
ዳያስፖራው ማህበረሰብ ከለውጡ በኋላ የህዳሴ ግድብ ግንባታ በሚፈለገው ደረጃ እና ጥራት እየተከናወነ ስለመሆኑ በቂ መረጃ እንዲያገኝ እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ወይዘሮ ሰላማዊት፤ በየሀገራቱ የሚገኙ ሚሲዮኖች እና በቪዲዮ የስልክ ግንኙነት በመታገዝ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለግድቡ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚያስችል ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
በተያዘው ዓመት ማጠቃለያ ላይም 200 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ እንችላለን በሚል መነሾ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል። የሦስት ወር አፈጻጸም እቅዱንም በሚፈለገው መጠን ለማሳካት የሚያስችል ተነሳሽነት መኖሩን እንዳመላከተ አስረድተዋል።
ዳያስፖራው ማህበረሰብ ከግድቡ ግንባታ በተጨማሪ ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ283 ሺህ ዶላር በላይ መለገሱን ወይዘሮ ሰላማዊት ገልጸዋል። ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች በ2013 በጀት ዓመት ከአንድ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ወይም 50 ሚሊዮን ብር ከዳያስፖራው ለመሰበሰብ የታቀደ መሆኑን ጠቁመው፤ ለዚህም በየሃገራቱ የሚገኙ አምባሳደሮች እና በኤጀንሲው በኩል በተገኙ አማራጮች ፕሮጀክቶቹን የማስተዋወቅ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ወይዘሮ ሰላማዊት ከሆነ፤ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቱ ይፋ ከተደረገ በኋላ በተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ሥር የዳያስፖራውን ተሳትፎ የሚያስተባብር ንዑስ ኮሚቴ ተቋቁሟል።
በአውሮፓ፣ አሜሪካ እና የተለያዩ ዓለማት ለሚገኙ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ስለፕሮጀክቱ አላማ እና የልማት አስፈላጊነትን በኢንተርኔት እና በአካል ጭምር በማግኘት ገለጻ እየተደረገ ይገኛል።
ለፕሮጀክቶቹ የተዘጋጀውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር የማስተዋወቅ ስራ እየተከናወነ በመሆኑ በቀጣይ ጊዜያት ለመሰብሰብ የታቀደውን 50 ሚሊዮን ብር አሊያም ከዚያ በላይ ገቢ ለመሰብሰብ የሚያስችል ጥረት በመደረግ ላይ ነው።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ ዳያስፖራው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በሚያስከብሩ እና ጥሪ በተደረገባቸው ጉዳዮች ላይ በስፋት እየተሳተፈ በመሆኑ ክብር እንደሚገባው ተናግረዋል። የህዳሴ ግድብ ግንባታ እና ከገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ተሳትፎ በተጨማሪ የኮቪድ -19 በሽታን ለመከላከል በተደረገው ጥረት ሀገርን ለመታደግ ጥረት እያደረገ ለሚገኘው የዳያስፖራ ማህበረሰብ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ለገበታ ለሀገር ዜጎች እያደረጉ ያሉት ድጋፍ አስደናቂ መሆኑንና እስካሁን ድረስ 283,378 ዶላር ያህል ገንዘብ ከዳያስፖራው መሰብሰቡን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ለዚህ ሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ከሰጡ ትውልደ ኢትዮጵያውያን መካከል አሥር የሚደርሱት በኅዳር አጋማሽ በሚካሄደው የገበታ ለሀገር መርሐ ግብር ላይ ሙሉ ወጫቸው ተሸፍኖ እንደሚጋበዙ አክለው ገልጸዋል።

(ኢፕድ)

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.