‹‹ የግብጹ ኢማም ኢትዮጵያ አባይን በብቸኝነት በመጠቀም ሌሎችን ለመጉዳት እየሰራች ነው ማለታቸው ከእውነት የራቀና ተቀባይነት የሌለው ነው›› – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

‹‹ የግብጹ ኢማም ኢትዮጵያ አባይን በብቸኝነት በመጠቀም ሌሎችን ለመጉዳት እየሰራች ነው ማለታቸው ከእውነት የራቀና ተቀባይነት የሌለው ነው›› – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት
የግብጹ ኢማም ሼክ አልሃዛር አህመድ ጦይብ ኢትዮጵያ የአባይን ወንዝ በብቸኝነት በመጠቀም ሌሎች ሀገራት ላይ ጉዳት ለማድረስ እየሰራች ነው ማለታቸው ከእውነት የራቀና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስታወቁ፡፡ ከምርጫ በኋላ የምትቀጥለውን ሀገር ከግል ጥቅም በማስቀደም ሁሉም ለሀገሩ ሰላም ዘብ እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ።
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር የግብጻዊውን ኢማም ንግግር አስመልክተው ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ኢማሙ ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝን በብቸኝነት በመጠቀም ሌሎች ሀገራት ላይ ጉዳት ለማድረስ እየሰራች ነው ብለው መናገራቸው ከእውነት የራቀና ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት አቋም ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ያማከለ አፍሪካዊ አስተሳሰብ መሆኑን የጠቆሙት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ፣ የግብፅና ሱዳን ለኔ ብቻ ባይነት ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አመልክተዋል። ኢማሙ የአረብ ሀገራት ከግብፅና ሱዳን ጎን እንዲቆሙ ያቀረበው ጥሪ ሃይማኖታዊ መሰረትና ተቀባይነት የሌለው መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በአባይ ውሃ ላይ የሚያደርገውን ልማት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እንደሚደግፈው የገለጹት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ፤ ኢትዮጵያ ግብጽንና ሱዳንን በማይጎዳ መልኩ በፍትሃዊነት የአባይን ውሃ ልጠቀም ማለቷ ትክክኛ አካሄድ እንደሆነም አመልክተዋል፡፡
የአባይን ውሃ ግብጽና ሱዳን ለብዙ ዓመታት በብቸኝነት ሲጠቀሙ መቆየታቸውን የጠቆሙት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትና ህዝብ ከአሁን በኋላ በብቸኝነት ልጠቀም፤ ወደ እናንተም አንለቅም ማለት ይችሉ ነበር፤ ይህን አላሉም፡፡ በፍትሃዊነት እንጠቀም ነው ያሉት ፤ ይህም ትክክለኛ አካሄድ ነው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥትና ህዝብ እያሉ ያሉት በድህነትና በጨለማ ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦች ልማትና ብርሃን ያግኙ ነው ፤ እናንተም ተጠቀሙ እኛም እንጠቀም ማለታቸው ትክክለኛ ብይን እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
ሁሉንም የተፋሰሱን ሀገራት ሊጠቅም የሚችለው ሀብት በጥቂት ሀገራት ተጠቃሚነት ብቻ መገደብ የለበትም፤ ግብጽ፣ ሱዳንና ለሌሎች የተፋሰሱ ሀገራትንም የሚጠቅመው የህዳሴ ግድብን በመደገፍ ተባብሮና ተጋግዞ ለማደግ እራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው ብለዋል፡፡
ሶስቱ ሀገራትም በመቀራርብ፣ በመነጋገርና በመመካከር ችግሩን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡
ምንጭ፡- አዲስ ዘመን ሰኔ 11 ቀን 2013 ዓ.ም

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.