የአረብ ሊግ የህዳሴው ግድብ በተመለከተ ያሳለፈው ውሳኔ ተቀባይነት የለውም-የኢትዮጵያ መንግስት - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የአረብ ሊግ የህዳሴው ግድብ በተመለከተ ያሳለፈው ውሳኔ ተቀባይነት የለውም-የኢትዮጵያ መንግስት
የአረብ ሊግ በህዳሴ ግድብ ላይ በኳታር ተወያይቶ ያሳለፈው ውሳኔ ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል መንግስት ኮንኖታል፡፡
ሚዛናዊነት የጎደለው እና ወደ አንድ ወገን ያደለ ወሳኔ እንደሆነ የኢትዮጰያ መንግስት መግለጫ አውጥቷል፡፡
የግብጽ እና የሱዳንን ቅሬታ ተቀብሎ ገምቢ ሚና ይጫወታል በሚል ሊጎ ቢጠበቅም፣ ውጤት አልባ እንዲሆን አድርጎታል ይላል መግለጫው፡፡
የህዳሴወን ግድብ አለማቀፋዊ እና የፖለቲካ እንድም እንዲኖረው ማድረግ በቀጠናው የአባይን ወንዝ በትብብር እና በዘላቂነት ለመጠቅም የሚያስችል መነገድ አይደለም ብሏል፡፡
የአርብ ሊግ አባል ሀገራት የአባይ ወንዝን አጠቃቀም እና የኢትዮጵያን የነበረ አቋም በሚገባ ማወቅ አለባቸው፡፡
በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ከድህነት የሚያወጣ፣የሀይል አቅርቦት፣የውሃ አቅርቦት እና የምግብ ዋስትና የምታረጋግጥበት ፕሮጅክት ነው፡፡
ኢትዮጵያ አለም አቀፉን የውሃ አጠቃቀም ህግን በማክበር የጎላ ጉዳት የማያመጣ የተፈጥሮ መብቷን ነው የተገበረቸው ነው ያለው መንግስት፡፡
የተፋሰሱ ሀገራት በትብብር እና በውይይት የውሃ ደህንነትን ማረጋገጫ መንገድ እንደሆን የኢትዮጵያ ጽኑ እምነት ነው፡፡
አባይ የጋራ ሀብት እንጂ የተናጠል የግብጽ እና የሱዳን ሀብት አይደለም ይላል መግለጫው፡፡
ለዚህ ነው የአረብ ሊግ ሚዛናዊነት የጎደለው ሌሎች የአባይ ባለቤት የሆኑ የተፋሰሱን ሀገራት ወደ ጎን በመተው ለሁለቱ ሀገራት ብቻ ያደላ አወዛጋቢ አቋም መያዙን መንግስት የሚኮንነው፡፡
ድርጅቱ በአባይ ጉዳይ ላይ ጥቅም የሌለው እና የተሳሰተ መንገድን መከተሉ ከዚህ የበለጠ ማሳይ አለመኖሩን የገለጸው መንግስት፤ኢትዮጵያ የሁለቱን ሀገራት ስጋት ግመት ውስጥ ያስገባ፣ የታችኞቹን የተፋሰስ ሀገራትን በጋራና በትብብር መንፈስ እንጠቀም ምርሆን ተግባራዊ ታደርጋለች፡፡
የህዳሴው ግድብ ጉዳይ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር የሚደረገውን ድርድር በሚገባ ሳያጤኑ የአረብ ሊግ አባል ሀገራት በውሳኔያቸውን በድጋሜ ያዩትል የሚል እምነት አለው፡፡
የህዳሴውን ግድብ አሞላልን በተመለከተ ሊጉ የያዘውን አቋም የኢትዮጵያ መንግስት ሙሉ ለሙሉ እንደማይቀበለው አስታውቋል፡፡
ከዚህ ይልቅ እንደ አንድ የቀጠናው ድርጅት ፣ሶስቱ ሀገራትን በጋራ ተጠቃሚ የሚያደርግ መፍተሄ በማምጣት የተዛባ እና ምክንያታዊ ያልሆነ አቋሙን እንዲያስተካክል መንግስት ጥሪ አቅርቧል፡:
ምንጭ፡-ኤፍ ቢ ሲ ሰኔ9/ 2013

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.