የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ምሁራን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ ያለውን ብዥታ የማጥራት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተጠቆመ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ምሁራን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ ያለውን ብዥታ የማጥራት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተጠቆመ

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ምሁራን በዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ ያለውን ብዥታ በሳይንሳዊ እውቀት እና በእውነት ላይ የተመሰረቱ መረጃዎችን በማቅረብ የማጥራት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተጠቆመ።

በጎንደር ዩንቨርሲቲ ‹‹የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዓለም አቀፍ የውሃ ሕግ ፣ሉዓላዊነት እና የግጭት አፈታት ›› በሚል ርዕስ አገር አቀፍ ኮንፍረንስ ሲጀመር በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የድንበር እና ድንበር ተሻጋሪ ሀብቶች የሚኒስቴር አማካሪ እና የኢትዮጵያ የድርድር ቡድን የሕግ አማካሪ አምባሳደር ኢብራሂም እድሪስ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት በአሁን ወቅት ታላቁን የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ግብጽና ሱዳን የጥቅም እና ፍላጎት በተፃረረ መልኩ አስገዳጅነት ያለው ስምምነት ለማድረግ በመትጋት ላይ ናቸው፡፡

በተሳሳተ አካሄድ አለም አቀፉን ማህበረሰብ በተለይ ምዕራባውያኑን ከጎናቸው ለማሰለፍ ጫናዎችን ለማሳደር ጥረት በማድረግ ላይ እንደሆኑ ያመለከቱት አምባሳደር ኢብራሂም፤ አለማቀፋዊ ጫናዎችን ለመቋቋም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምሁራን ሚና ትልቅ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡

በተለይም በአሁን ወቅት‹‹ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ምሁራን በዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ ያለውን ብዥታ በሳይንሳዊ እውቀትና በእውነት ላይ የተመሰረቱ መረጃዎችን በማቅረብ የማጥራት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

የህዳሴ ግድብን በሚመለከት ግብጾች የሚራመዱበት መንገድ እውነትን የያዘ እንዳልሆነ ያስገነዘቡት አምባሳደር ኢብራሂም አካሄዶቹ ከፍትሕ ፣ከሞራል ፣ከሕግ ጋር የሚቃረኑ እንደመሆናቸው በእኛ በኩል ያለውን እውነት በማስረዳት ረገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ምሁራኖቻችን ግዴታና ኃላፊነት አለባቸው ከዚህ የበለጠ ብሔራዊ ሥራ አመልክቷል፡፡

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ዲንና መምህር አቶ ልጃለም ጋሻው በበኩላቸው በአባይና በህዳሴ ግድብ ላይ በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ የሚስተዋሉ የግንዛቤ ክፍተቶች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ምሁራኖች በቂ ስራ ያለመስራታቸው ውጤት ሆኖ የሚጠቀስ መሆኑን ገልጸዋል።

እነዚህን የግንዛቤ ብዥታዎች በማጥራት ረገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራኖች ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ይህ እንደመሆኑም ጥናትና ምርምርን መሰረት ባደረገ መልኩ ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ያሰበቻቸውና እየሰራቻቸው የሚገኙት ስራዎች የማንንም መብት እንደማይጋፋ ፣አብሮ የመበልጸግ፣ አብሮ የማደግ ፍላጎት እንዳላት ይሄም ብሔራዊ መብቷ መሆኑን እንዲሁም የሉዓላዊነት ጉዳይ እንደሆነ በትክክል ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ማስረዳት ማሳወቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

‹‹የአባይ ጉዳይ የውሃ ጉዳይ ብቻ አይደለም ፤የኢትዮጵያ እድገት ፣የብልጽግና በር ቁልፍ ነው›› ያሉት አቶ ልጃለም፣ሁሉም ማህበረሰብ ፣ተቋም ፣ዜጋ ግዴታውን መወጣት እንዲችል በማንቃት እንዲሁም ከውጪ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ተገቢ በሆነ መልኩ ምሁራዊ ምላሾችን በመስጠት ረገድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ምሁራን ያለባቸውን ትልቅ ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው አስገነዝበዋል፡፡

በዚህ ረገድ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ባለሙያዎች በተገኘው አጋጣሚ የድርሻቸውን ለመወጣት በምርምር ስራ ፣በሳይንስ እና በዲፕሎማሲው ላይ የድርሻቸውን እየተወጡ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አጸደወይን ‹‹በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ያለውን መጓተት ወደ ትክክለኛው መስመር በማምጣት ረገድ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን፤ የአፍሪካ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ምሁራን ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው››ብለዋል

የሌሎችን አህጉራት ተሞክሮ በመጥቀስ፣የአፍሪካ ምሁራን በተለይ በአገራት መካከል ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖር የኢኮኖሚ ትስስር እንዲጎለብትና የሕዝብ ለሕዝብ አንድነትና ግንኙነት እንዲጠናከር የሚያግዙ ተግባራትን በማከናወን ረገድ ከፍተኛ ሚና መጫወት እንደሚጠበቅባቸውም አስታውቀዋል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በበኩላቸው፤ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ምሁራን የህዳሴው ግድብ መሰረት ከተጣለበትና ከዲዛይን ጀምሮ ከፍተኛ የእውቀትና የክህሎት ጉዳዮችን በማፍለቅ አስተዋጽዖ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡ይሑንና ከህዳሴው ግድብ ጋር ተያይዞ በውጪ ኃይሎች የሚደረገውን ጫና ለመመከት በሚደረገው ርብርብ ላይ ያላቸው ተሳትፎ በቂ ነው ለማለት የማያስደፍር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በተለይ በአሁን ወቅት ‹‹ከአባይ ጋር ተያይዞ የሚወጡ የተዛቡና የተጣመሙ አካሄዶችን በእውቀትና በእውነት መሞገት እንዲሁም ፤ከመቼውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ የጋራ ድምጽ ማሰማት የግድ ይላል ›› ያሉት ሚኒስቴር ዴኤታው፣ የኢትዮጵያ ምሁራኖቻችን በዓለም አቀፍ መጽሔቶች እውነትና እውቀትን መሰረት በማድረግና ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ስለ አባይ መጻፍ ፣መሞገት ፣ምላሾችን መስጠት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል ፡፡ በዚህ አግባብም‹‹ከህዳሴው ግድብ ጋር ተያይዞ የሚሰነዘሩ ጫናዎች መመከት አለባቸው›› ብለዋል ፡፡

ምንጭ፡-አዲስ ዘመን ግንቦት 4 ቀን 2013 .

 

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.