የመገናኛ ብዙሃን ስለ ሕዳሴ ግድብ ትክክለኛውን መረጃ ለሕዝቡና ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ በሚፈለገው ልክ በመስጠት ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ። - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የመገናኛ ብዙሃን ስለ ሕዳሴ ግድብ ትክክለኛውን መረጃ ለሕዝቡና ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ በሚፈለገው ልክ በመስጠት ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ።

የመገናኛ ብዙሃን ስለ ሕዳሴ ግድብ ትክክለኛውን መረጃ ለሕዝቡና ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ በሚፈለገው ልክ በመስጠት ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ።
የሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤትና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ‘የመገናኛ ብዙሃን ሚና ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ’ በሚል የምክከር መድረክ አካሂደዋል።

መድረኩ ባለድርሻ አካላትና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን ያሳተፈ ነው።

የግድቡ አሁናዊ የአፈጻጸም ደረጃና ይህን ተከትሎም ሁለተኛውን የውሃ ሙሌት ለማካሄድ በሚደረገው ጥረት የመገናኛ ብዙሃን ሚናቸውን እንዴት ሊወጡ እንደሚገባ ተነስቷል።

የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ መገናኛ ብዙሃን ከምን ጊዜውም በላይ ስለ ሕዳሴ ግድብ ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

“የሕዳሴ ግድብ ጉዳይ የኢኮኖሚ ነጻነት ጉዳይ ነው” ያሉት ዶክተር አረጋዊ በዚህ ረገድ ሚዲያው መርህን በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር በመጫወት ሚናውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አበራ ወንደሰንም የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ሊካሄድ መሆኑን ተከትሎ የዲፕሎማሲ ጫናዎችን መቆጣጠር የሚያስችል የመረጃ ስርጭትና ትብብር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ሂደቱ እንዳይሳካ የሚሹ ሃይሎች በአገሪቷ ሠላምና መረጋጋት እንዳይኖር በበይነ-መረብ መገናኛ ብዙሃንና በተለያዩ ማህበራዊ ድረ-ገጾች እየሰሩ መሆኑንም አንስተዋል።

በመሆኑም ይህን ለመቀልበስና በአገሪቷ ሠላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የመገናኛ ብዙሃን ሚና ከፍያለ መሆኑን ገልጸዋል።

በተፋሰስ ልማት ባለስልጣን የድንበርና ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ በላይነህ ተመስገን በበኩላቸው በግድቡ ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ የዲፕሎማሲ ጥረቶች እንዲሳኩ ሚዲያው የራሱን ድርሻ መወጣት እንዳለበት አንስተዋል።

ሚዲያው የኢትዮጵያን በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሰረተ አካሄድ ለዓለም ማስረዳት ይኖርበታል ብለዋል።

አሁናዊ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደት 80 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን በመጪው ክረምትም ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት የሚከናወን እንደሆነ መገለጹ ይታወሳል።
ምንጭ፡- ኢዜአ

 

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.