አሜሪካንን ጨምሮ ሌሎች ሃያላን የሚባሉ አገራት በኢትዮጵያ ላይ ለማሳረፍ የሚሞክሩት ጫና የተለመደና ሁሌም ቢሆን የሚያደርጉት በመሆኑ ብዙም መገረም እንደማይገባ የትግራይ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበርና የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ አስገነዘቡ ። - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

አሜሪካንን ጨምሮ ሌሎች ሃያላን የሚባሉ አገራት በኢትዮጵያ ላይ ለማሳረፍ የሚሞክሩት ጫና የተለመደና ሁሌም ቢሆን የሚያደርጉት በመሆኑ ብዙም መገረም እንደማይገባ የትግራይ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበርና የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ አስገነዘቡ ።

ዶክተር አረጋዊ በተለይም ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፣ አሜሪካንን ጨምሮ ሌሎች ሃያላን የሚባሉ አገራት በኢትዮጵያ ላይ ለማሳረፍ የሚሞክሩት ጫና የተለመደና ሁሌም ቢሆን የሚያደርጉት ቢሆንም አሁን እያደረጉ ያለው ጫና ለየት የሚያደርገው ኢትዮጵያ በተቻለ መጠን ፍትሀዊ የሆነ የሕግ ማስከበር ሥራ እየሠራች ባለችበት ጊዜ መሆኑ ነው ።

መንግሥት በትግራይ ክልል እያደረገ ያለው ጦርነት ሳይሆን የሕግ ማስከበርና ጥፋተኞች (ወንጀለኞችን) አድኖ ለፍትህ የማቅረብ ሥራ ነው ያሉት ዶክተር አረጋዊ፣ ይህ ሆኖ ሳለ አገሪቱን ወደኋላ ለመጎተት ያልተገቡ ውሳኔዎችን የሚያሳልፉ ሃያላን አገራትን ሕዝብና መንግሥት ተባብሮ እንደሚቋቋማቸው ጠቁመዋል።

የአሜሪካን ሴኔት ያሳለፈው ውሳኔ አላማው በኢትዮጵያ ላይ ጫና መፍጠር ነው፤ ይህ ደግሞ ጁንታውን ቡድን የሚደግፍ ውሳኔ ከመሆኑም በላይ የሌሎች ተቀናቃኝ ጎረቤት አገሮች ለማስደሰት ወይም እነሱን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ነው፤ የትም አይደርስም ብለዋል።

የእነሱ ተጽዕኖ ምናልባትም ከሚሰጡን ብድርና ዕርዳታ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ህዝቡ የጀመረው የልማት እና የዴሞክራሲ ግንባታ በራሱ ወደፊት የሚያስቀጥለን በመሆኑ ያን ያህል የሚያሳስብ እንደማይሆን አመልክተዋል።

ለዚህም በተለይ ህዝቡና መንግሥት በራሳችን አቅም የጀመሩት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የግንባታ ሥራ ተጠቃሽ ነው ያሉት ዶክተር አረጋዊ ፣ይህንን ግድብ በተያዘለት ጊዜ ሠርቶ ማጠናቀቅ የእነሱን የተጽዕኖ ዋጋ ያሳጣዋል፤ በመሆኑም ከዚህ በኋላም ቢሆን አንድነታችንን አጠናክረን በተለይም የግድብ ግንባታ ሥራችንን ዳር ካደረስን ምንም ዓይነት ጠላት እኛን ማንበርከክ አይችልም ብለዋል።

አገርን ከፍ ለሚያደርግና አንገታችንን ቀና አድርገን ከእነሱ እኩል እንድንሆን የሚያደርገንን የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሥራ አጠናክረን መቀጠል ከቻልን የእነዚህ አካላት ተጽዕኖ ፋይዳ ቢስ እንደሚሆንም ጠቁመዋል።

ምዕራባውያኑ በተደጋጋሚ ተደራደሩ አሁን ደግሞ ይባስ ብለው በሁለት ወገን የተከፈተ ጦርነት በሌለበትና እየተከናወነ ያለው ሥራ ሕግ ማስከበር እንደሆነ እያወቁ ተኩስ አቁሙ ማለታቸው ሌላ ምንም ሳይሆን ከዚህ ቀደም የጁንታው አባላት ተላላኪዎቻቸው ስለነበሩ እነሱን ወደሥልጣን ለመመለስና ራዕያቸውን ለማሳካት የሚሄዱበት መንገድ እንደሆነ ገልፀዋል።

እንደ ዶክተር አረጋዊ ገለፃ፣ እነሱ እንዲህ የሚሆኑላቸው ህወሓቶች እራሳቸው ከማንም ጋር አንደራደርም በማለት በመከላከያ ሃይላችን ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። ሕገ መንግሥቱን በጣሰ መልኩ ምርጫ አድርገው በራሳቸው መንገድ ሲጓዙም ነበር፤ አሁንም እንደ አላማ አድርጎ የሚንቀሳቀሱት ትግራይን ለመገንጠል ነው፤ ይህ በሆነበት ሁኔታና በሽብር በተመዘገበ ቡድን ጋር ተደራደሩ እያሉ የሞተ ነገር ማንሳታቸው በጣም የሚያሳዝንና ተቀባይነት የሌለው ቀልድ እንደሆነ አስታውቀዋል።

ምዕራባውያኑ ፍላጎታቸው የጁንታውን ቡድን አባላት በሚያሳድሩት ጫና ምክንያት መንግሥትን በማዳከም እነሱን ዳግም ወደ ሥልጣን ማማ ላይ ማውጣት ነው፤ ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ ከሽብርተኛ ቡድን ጋር የሚደራደር ህዝብም ሆነ መንግሥት አይኖርም ብለዋል።

መንግሥት ከዚህ በፊትም ቢሆን ጠንከር ያለ እርምጃን መውሰድ በነበረበት ወቅት ባለመውሰዱ ነው

ሁሉ ችግር ተከስቷል ያሉት ዶክተር አረጋዊ፣ አሁንም ጠንከር ብሎ መርሃዊ የሆነ አቋም ይዞና ህዝቡን አሰባስቦ ወደፊት መግፋት እንደሚጠበቅበት አመልክተዋል።

ምንጭ፡-አዲስ ዘመን ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ.ም

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.