‹‹ሱዳኖች ከሚጣረሱ አስተያየቶች ወጥተው በአፍሪካ ህብረት የሚደረገውን ድርድር መደገፍ አለባቸው›› – አቶ ዘሪሁን አበበ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲፕሎማትና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኮሚቴ የኢትዮጵያ አባል - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

‹‹ሱዳኖች ከሚጣረሱ አስተያየቶች ወጥተው በአፍሪካ ህብረት የሚደረገውን ድርድር መደገፍ አለባቸው›› – አቶ ዘሪሁን አበበ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲፕሎማትና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኮሚቴ የኢትዮጵያ አባል

ሱዳኖች የሚጣረሱ አስተያየቶች ከመስጠት ወጥተው በአፍሪካ ህብረት የሚደረገውን ድርድር በመደገፍ ለስኬታማነቱ ጥረት ቢያደርጉ ሕዝባቸውንም ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲፕሎማትና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኮሚቴ የኢትዮጵያ አባል አቶ ዘሪሁን አበበ ገለጹ።

አቶ ዘሪሁን በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ የሱዳን መንግሥት ከሚጣረሱ አስተያየቶችና መግለጫዎች መውጣት አለበት። በአፍሪካ ህብረት የሚደረገውን ድርድር በመደገፍ ለሱዳን ህዝብ ዘላቂ ጥቅም ሊሰራ ይገባል።

ኢትዮጵያ ከመጀመሪያውም በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ የሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር እንዲሳካ ከፍተኛ ጥረት እያደረገች በቅን ልቦና እየተንቀሳቀሰች መሆኗን አስታውቀዋል

ለኢትዮጵያ የታላቁ የህዳሴ ግድብ አገራዊ ፕሮጀክቷ ነው፤ በአባይ ተፋሰስ ደንብና ባህል ሆኖ የቆየውን የአገራቱን በተናጠል የመንቀሳቀስ አካሄድ በመቀየር ‹‹ለትብብር መትጋት አለብን›› በሚል ከመጀመሪያው ጀምሮ በግድቧ በብሄራዊ ፕሮጀክቷ ላይ መነጋገር ጀምራለች። ይሄ ታይቶና ተደርጎ የማይታወቅና ሊያስመሰግናት የሚገባ ነው ብለዋል።

እንደ ግርጌ ተፋሰስ አገርነታቸው ሱዳኖች ለትብብር መትጋት አለባቸው ያሉት አቶ ዘሪሁን፤ ሱዳኖች ይህንን ዕድል ከማበላሸት ይልቅ ሊጠቀሙበት ይገባል። አዲስ የትብብር ምዕራፍ መከፈቱ ለቀጠናውም ለአገሪቱም እጅግ እንደሚጠቅም አመልክተዋል።

በቅን ልቦና ለትክክለኛ ትብብር የሚደረግ ውይይት መፍትሄ ያመጣል፣ መፍትሄውም ዘላቂነት ይኖረዋል ያሉት አቶ ዘሪሁን፤ ‹‹አባይ አውሮፓዊ፣ አሜሪካዊ ወይንም አረባዊ ወንዝ አይደለም። እንደ አንድ አፍሪካዊ ወንዝና አገራቱም አፍሪካዊ እንደመሆናቸው መጠን የአፍሪካ ህብረት ድርድር ሂደት እንዲሳካ ማድረግ ከሱዳኖች ይጠበቅባቸዋል›› ብለዋል።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ለማን ጥቅምና ፍላጎት እንደሆነ ባናውቅም ግድቡ በአንድ በኩል ከፍተኛ ጥቅም እንደሚሰጥ እየተናገሩ በሌላ በኩል ደግሞ ይህንኑ እውነታ የሚጻረሩ ሀሳቦችን ሲያንጸባርቁ እንደሚሰሙ አመልክተዋል።

ግድቡ ለሱዳን ፈርጀ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቁመው፤ በመንግሥትና በከፍተኛ ትምህርት ተቋሞቻቸው ያጠኗቸውም ጥናቶች ይህንን ሃቅ በተጨባጭ እንደሚያረጋግጡ ጠቁመዋል።

ግድቡ ለሱዳን ያለው ጥቅም ከፍተኛ በመሆኑ ለኛ የሚያሳስበን አይደለም። ፍትሃዊና ትክክለኛ አቋማችንን እኛም በተለያዩ መንገዶች እየገለጽን እንገኛለን፣ ይህንንም አጠናክረን እንቀጥላለን። በኢትዮጵያ ላይም የተለየ የሚፈጥረው ነገር እንደሌለ አስታውቀዋል።

‹‹የሱዳን ወገን አንደኛው ሚኒስትር የሆነ ነገር ሲል ሌላኛው ሚኒስትር ደግሞ ሌላ ነገር ያነሳል። የትኛው ትክክለኛ የሱዳን አቋም እንደሆነ አይታወቅም›› ያሉት አቶ ዘሪሁን፤ በቅርብ ጊዜ እንዳየነው የሱዳን ወገን የታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የአፍሪካ ህብረት ድርድሩን ለማስቀጠል ያደረገው ሙከራ ውጤት እንዳይኖረው አድርገዋል።

ይህ በሆነበት ሁኔታ ተመልሰው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ግድቡን በተመለከተ የአፍሪካ ህብረት የሚያደርገውን ጥረት እናደንቃለን የሚል ነገር ተናግረዋል። እነዚህ እርስ በእርሳቸው የሚጣረሱ ጉዳዮች እንደሆኑ አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ ትናንት የነበራት፣ አሁንም የያዘችውና አጠናክራም የምትቀጥልበት ትክክለኛ ብላ የምታስበው አቋሟ ዋናው የግድቡ ጉዳይ ከቴክኒክ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ናቸው መፈታት የሚችለውም በሶስቱ አገራት ውይይትና ምክክር ነው ብለዋል።

 

ምንጭ፡- አዲስ ዘመን ግንቦት 15 ቀን 2013 .

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.