“ደቡብ ሱዳን የናይል ማዕቀፍን ለማጽደቅ መፈለጓ የቅኝ ግዛት ውልን ታሪክ ለማድረግ ትልቅ አቅም ይፈጥራል ”- አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

“ደቡብ ሱዳን የናይል ማዕቀፍን ለማጽደቅ መፈለጓ የቅኝ ግዛት ውልን ታሪክ ለማድረግ ትልቅ አቅም ይፈጥራል ”- አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ

ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍን በፓርላማዋ ለማጸደቅ መፈለጓ ግብጽና ሱዳን በአባይ ወንዝ ላይ የያዙትን የቅኝ ግዛት ውል ታሪክ ለማድረግ ትልቅ አቅም የሚፈጥር እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስታወቁ።

አምባሳደር ዲና ሚፍቲ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ የናይል ተፋሰስ ትብብር ማዕቀፍን የፈረሙ ሀገራት ስድስት ናቸው። አራቱ በፓርላማቸው አጽድቀውታል። አሁን ደቡብ ሱዳን የአባይ ትብብር ማዕቀፍ በፓርላማ እንደምታጸድቅ ማስታወቋ ግብጽና ሱዳንን በዋናነት ተጠቃሚ ሲያደርግ የቆየው የቅኝ ግዛት የአባይ ስምምነትን ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ለማድረግ ትልቅ አቅም ይፈጥራል።

ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን የማጽደቅ ሂደት የቅኝ ግዛት የውሃ ክፍፍል ውልን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በማስወገድ ታሪክ ለማድረግ ለሚደረገው ጥረት ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው።

ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስታጸድቀው ማዕቀፉን ያጸደቁ ሀገራት ቁጥር ወደ አምስት ከፍ ይላል፤ በቀጣይም ሌሎች ሀገራትም ያጸድቁታል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህ መሰረት የተፋሰሱ አባል ሀገራት መካከል አብላጫዎቹ ሲያጸደቁት የአባይ ወንዝ የቅኝ ግዛት ውል በመተው ፍትሃዊነት ላይ የተመሰረተውን የኢንቴቤ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ አቅም ይፈጠራልብለዋል።

የአባይ ወንዝ ተፋሰስ ሀገራት በጎረቤትነት የተሳሰሩ እና ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ናቸው ያሉት ቃል አቀባዩ፤ የትብብር ማዕቀፍ በተፋሰስ ሀገራቱ መካከል የናይል ወንዝን በፍትሃዊነት አብሮ ለመጠቀም የሚረዳ ሰነድ በመሆኑ ከጊዜ ወደጊዜ ተቀባይነቱ ከፍ እያለ መምጣቱን አስታውቀዋል።

አምባሳደር ዲና እንዳስታወቁት፤ ስምምነቱ በጋራ ተጠቃሚነት እና በምክንያታዊነት ላይ የተመሰረተ ልማትን የሚደግፍ እና በአባይ ወንዝ ላይ ቀደም ብሎ የተዘጋጁ የቅኝ ግዛት ውሎችን የሚተካ ነው። ይህን ስምምነት አንዳንድ ሀገራት ፈርመው በፓርላማቸው ግን ሳያጸድቁት ወጥተዋል።

ግብጽና ሱዳንም በመጀመሪያ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነቱን ለማዘጋጀት በተደረገው የድርድር ሂደቱ ላይ ላይ የነበሩ ቢሆንም በኋላ ላይ ግን ከድርድሩ በመውጣታቸው በማዕቀፉ አልፈረሙም።

የታችኞቹ የተፋሰስ ሃገራት የውሃውን አጠቃላይ ሃብት ለግብጽና ለሱዳን የሚያከፋፍለውን እና በእንግሊዞች አማካኝነት የተፈረመውን የቅኝ ግዛት ውል ለመተው ባለመፈለጋቸው የትብብር ማዕቀፉን አልደገፉትም። ይሁንና ኢትዮጵያም ሆነች ሌሎቹ የተፋሰሱ ሀገራት ከውሃው ሃብት የመጠቀም መብት ስላላቸው በእኩልነት ላይ የተመሰረተውን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ወደስራ ለማስገባት ስምምነት አድርገው እየሰሩ ይገኛል ብለዋል።

የናይል ተፋሰስ ሀገራት ትብብር ኢትዮጵያ ግብፅ እና ሱዳንን ጨምሮ አሥር አባላት ያሉት ሲሆን፤ ኤርትራን በታዛቢነት ይዟል። ሀገራቱ በወንዙ ላይ ለሚኖራቸው ፍትሀዊ ተጠቃሚነት የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት አዘጋጅተዋል ስምምነቱን ስድስት ሀገራት ሲፈርሙ ከዚህ ውስጥ ኢትዮጵያ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ዩጋንዳ ስምምነቱን በፓርላማቸው አጸድቀውታል።

ምንጭ፡- አዲስ ዘመን ግንቦት 15 ቀን 2013 .

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.