የህዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት በተያዘለት ጊዜ ይካሄዳል – አቶ ደመቀ መኮንን - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የህዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት በተያዘለት ጊዜ ይካሄዳል – አቶ ደመቀ መኮንን

የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በተያዘለት ጊዜ እንደሚካሄድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

በጎረቤት ሃገራትና ታላላቅ ሃይቆች ክልል የሚገኙ የኢፌዴረ ሚሲዮኖች ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤትጋር በመተባበር “የናይል ፍትሃዊ አጠቃቀም፣ የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ለክልላዊ ትብብር ያለው ሚና” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው የበይነ መረብ ውይይት ላይ ተሳትፈዋል።

የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በሶስቱ ሃገራት የተመራማሪዎች ብሄራዊ ቡድን በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንደሚካሄድ አቶ ደመቀ መኮንን ገልፀዋል።

የሶስትዮሽ ድርድሩ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ መርህ መሰረት ውጤታማ እንዲሆን የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ያላቸውን እምነት አረጋግጠዋል።

ግብፅና ሱዳን ጉዳዩን ዓለም አቀፋዊ በማድረግ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ጥረት እያደረጉ ስለመሆኑም አውስተዋል።

በስብሰባው ተሳታፊ የነበሩት የደቡብ ሱዳን ምክትል የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ጉዳዮች ሚኒስትር ደንግ ዳው ደንግ በበኩላቸው ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ የሰላም ፕሮጀክት መሆኑን አውስተዋል፡፡

የሀገራቸው ፓርላማ በቅርቡ የናይል ስምምነት ማዕቀፍን እንደሚያፀድቅ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የሶሰትዮሽ ድርድር ሁሉን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ላይ በመድረስ እልባት እንደሚያገኝ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

በወቅቱም የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋውና ሌሌች የዘርፉ ባለሙያዎች የውይይት መነሻ ፅሑፍ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ምንጭ፡- ኤፍ.ቢ.ሲ

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.