የግድቡን ውሃ ጉዳይ የዓረብ አገራት አጀንዳ አድርጎ ለማቅረብ የሚሞከር አካሄድ ስህተት መሆኑ ተገለፀ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የግድቡን ውሃ ጉዳይ የዓረብ አገራት አጀንዳ አድርጎ ለማቅረብ የሚሞከር አካሄድ ስህተት መሆኑ ተገለፀ

ጉዳዩም በድርድር እንጂ በግጭት አይፈታም
የህዳሴ ግድብን ውሃ ጉዳይ የዓረብ አገራት አጀንዳ አድርጎ ለማቅረብ የሚሞከር አካሄድ ስህተት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ የህዳሴው ግድብ ጉዳይ በድርድር እንጂ በግጭት የሚፈታ አይደለም ሲልም አስታውቋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ትናንትና በሰጡት መግለጫ አንዳስታወቁት፤ የህዳሴ ግድብን የውሃ ጉዳይ የዓረብ አገራት አጀንዳ ለማድረግ የሚደረግ ጥረት ስህተት መሆኑ መታወቅ አለበት።
እንደ አምባሳደር ዲና ገለፃ፤ በዓባይን ወንዝ ጉዳይ አጀንዳው ወደማይመለከተው አካል ይዞ ለመሄድ የሚደረገው ጥረት ፍጹም ተቀባይነት የለውም። በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ሦስቱ አገራት (የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ) የሚያካሂዱት ድርድር የሚፈታው በሌሎች አካላት ሳይሆን በአፍሪካ ሕብረት ማዕቀፍ ውስጥ መሆን አለበት የሚለው የኢትዮጵያ የፀና አቋም አሁንም እንደተጠበቀ ነው።
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የሱዳን ወታደራዊ ክንፍ የሌሎችን አገራት መልዕክት ይዞ በመንቀሳቀስ የግድቡን አጀንዳ ወደ ሌሎች አገራት የመውሰድ አዝማሚያ ማሳየቱን የተናገሩት አምባሳደር ዲና፤ ሱዳን የራሷ አጀንዳ ሳይኖራት ስለግድቡ ጉዳይ የተሳሳተ አቋም መያዟ ስህተት መሆኑን ገልፀዋል።
ሱዳንም ሆነች ግብጽ ከኮንጎ ኪንሻሳው የግድቡ ውይይት ሲመለሱ ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር ወደ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ደብዳቤ መጻፋቸውን አስታውቀው፤ የግድቡ ጉዳይ በጦርነት እና በግጭት ሳይሆን በውይይት ብቻ ሊፈታ የሚችል አጀንዳ መሆኑን ገልፀዋል።
በዲፕሎማሲው መስክ ምንም አይነት ፉከራ አይመከርም ያሉት አምባሳደር ዲና፤ የዲፕሎማሲ ሂደት ሲሟጠጥ መጨረሻው ጦርነት ሊሆን ቢችልም፣ ጦርነት ላይም ዲፕሎማቶች ያስፈልጋሉ ሲሉ አስረድተዋል። የግብጽ እና የሱዳን መሪዎች ግን በኢትዮጵያ ጉዳይ ብዙ ጊዜ መፎከርና ማስፈራራትን እንደሚመርጡ ተናግረዋል።
ይሁንና የውሃ ጉዳዮች በጦርነት መፍትሄ የሚገኝላቸው ባለመሆኑ ለሰላማዊ ውይይት መጠናከር የሚችልበትን መንገድ ማሰብ እንደሚገባ አስረድተዋል።
በሌላ በኩል የሱዳኑ ሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ፤ ለኢትዮጵያ እና ለግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ያቀረቡት በዝግ እንወያይ ጥያቄ የኢትዮጵያ መንግሥት በቀጣይነት ሊያየው የሚችል ጉዳይ መሆኑን አስታውቀዋል።
ምንም ይሁን ምን ግን የህዳሴው ግድብ የድርድር ጉዳይ በአፍሪካ ማዕቀፍ ውስጥ ሊፈታ የሚችል እንደሆነ ኢትዮጵያ እምነት እንዳላት አምባሳደር ዲና አጽንኦት ሰጥተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትግራይ የሰብአዊ መብት ድጋፍ በተመለከተ የተናገረችውን ያክል ያደረገችው አሜሪካ ናት በማለት ምስጋና አቅርቧል።
*****************
(ኢ ፕ ድ)

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.