የሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ስብሰባን የተመለከተ ገለጻ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ለሆኑ የአፍሪካ አምባሳደሮች ተሰጠ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ስብሰባን የተመለከተ ገለጻ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ለሆኑ የአፍሪካ አምባሳደሮች ተሰጠ

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ሚኒስትሮች ስብሰባ በተመለከተ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ ለሆኑ የአፍሪካ አገሮች አምባሳደሮች ገለጻ አድርገዋል።

ገለጻው በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ ኪኒሻሳ በአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ ስር የተካሄደውን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ስብሰባን የተመለከተ ሲሆን÷ በስብሰባው ውይይት የተደረገባቸውን ጉዳዮች እና የኢትዮጵያን ዕይታ ለአምባሳደሮቹ ገለጻ ተደርጓል።

ኢትዮጵያ በሶስቱም ሀገሮች ተቀባይነት ያለው ስምምነት ላይ ለመድረስ በአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ ስር የሚደረገው ድርድር መቀጠል እንዳለበት በጽኑ እንደምታምን ተገልጿል።

ሶስቱ ሀገራት የአባይን ውሃ አጠቃቀም በተመለከተ ያላቸው አማራጭ በትብብር እና በአፍሪካዊ ወንድማማችነት ስሜት በጋራ መስራት እንደሆነ ለአምባሳደሮቹ አስረድተዋል።

ድርድሩን ስኬታማ ለማድረግ እና መተማመንን ለማጎልበት በአውሮፓውያኑ በጁላይ 2020 በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የቢሮ ስብሰባ ወቅት በተደረሰው መግባባት እና በወጣው መግለጫ መሰረት በሁለት ደረጃ፣ በቅድሚያ በግድቡ የመጀመሪያ ሙሌት እና ተያያዥ የውሃ አለቃቀቅ ጉዳዮች እና በመቀጠልም ሁሉን አቀፍ የውሃ አጠቃቀም ስምምነት ማድረግ የተሻለ አማራጭ እንደሆነ ኢትዮጵያ እንደምታምን ገልጸዋል።

በቀጣዩ ሐምሌ ወር የሚደረገውን የሁለተኛ ዓመት ሙሌት አስመልከቶ ኢትዮጵያ ለሱዳን እና ግብጽ የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ በቅን ልቦና ተነሳሽነቱን በመውሰድ በውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር በኩል ለግብጽ እና ሱዳን አቻዎቻቸው ደብዳቤ የተላከ መሆኑ ተገልጿል።

 

ሚኒስትሩም ግብጽና ሱዳን የህዳሴውን ግድብ የአረብ አገሮች የውሃ ደህንነት ስጋት አድርገው የሚያቀርቡት ሁኔታ እንዳሳዘናቸው ገልጸው÷ የአባይ ተፋሰስ አገራት ሁሉ አፍሪካዊ ሆነው ሳሉ ጉዳዩን ለፖለቲካ ጠቀሜታ ሲባል የሚያራምዱት አቋም ተቀባይነት የሌለውና ሁሉም በአጽንኦት ሊገነዘበው እንደሚገባ አሳስበዋል።

ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ወቅታዊ የድርድር ሁኔታ በተጨማሪ ለአምባሳደሮቹ የኢትዮጵያ-ሱዳን ወቅታዊ የድንበር ሁኔታን በተመለከተ፣ ኢትዮጵያ ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ በሁለቱ ሀገራት መካከል በተደረጉ ስምምነቶች እና ባሉት የድንበር አሰራር ማዕቀፎች አማካኝነት በድርድር ለመፍታት ያላትን ቁርጠኝነት ገልጻለች።

አምባሳደሮቹም በበኩላቸው ÷ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ድርድሩ በአፍሪካ ሕብረት ማዕቀፍ ስር “አፍሪካዊ መፍትሔ፣ ለአፍሪካ ችግር” በሚለው መርህ መሰረት ውጤታማ እንዲሆን ማስቻል እንደሚገባ ገልጸው ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን በዚሁ ማዕቀፍ ድርድራቸውን እንዲቀጥሉ አበረታተዋል።

የኢትዮጵያ-ሱዳን ድንበርን በተመለከተ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ ችግሮቹን ለመፍታት የወሰደችውን አቋም እንደሚያደንቁ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.