“ኢትዮጵያ ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት በኩል እንዲካሄድ የያዘችው አቋም ለህብረቱ ያላትን ክብርና እውቅና የሚያሳይና የሚደነቅ ነው” - አቶ መሀመድ አል - አሩሲ አክቲቪስትና የፖለቲካ ተንታኝ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

“ኢትዮጵያ ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት በኩል እንዲካሄድ የያዘችው አቋም ለህብረቱ ያላትን ክብርና እውቅና የሚያሳይና የሚደነቅ ነው” - አቶ መሀመድ አል - አሩሲ አክቲቪስትና የፖለቲካ ተንታኝ

ኢትዮጵያ ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ በሚል የሦስትዮሽ ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት እንዲካሄድ የያዘችው የጸና አቋም ለህብሩ ያላትን ክብርና እውቅና የሚያሳይና የሚደነቅ መሆኑን ታዋቂው አክቲቪስት እና የፖለቲካ ተንታኝ አቶ መሀመድ አል- አሩሲ አስታወቀ።

በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያን ወክሎ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ በመከራከር የሚታወቀው አቶ መሀመድ አል-አሩሲ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረገው ቃለምልልስ እንዳስታወቀው ፤ ኢትዮጵያ የታላቁን ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የሚነሱ ችግሮች በአፍሪካውያን እንዲፈታ የምታደርገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ለአፍሪካውያን አብሮነት መጠናከር እንዲሁም ችግራቸውን በራሳቸው መፍታት እንደሚችሉ ጥልቅ መነቃቃት እንዳላት ማሳያ ነው።

የአፍሪካ ችግሮች መፈታት ያለባቸው በአፍሪካ ነው። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ እንዲመጣ እያደረገችው ያለው ሁለንተናዊ ጥረት የሚደነቅና የሚያስመሰግናት ነው። ከዛም በላይ ለአፍሪካ ኅብረት ያላትን እውቅናና ክብር የሚያሳይ እንደሆነ አስታውቋል።

‹‹ገመናችንን፤ ችግራችንን ውጭ ማውጣት ትልቅ ውርደት ነው። እንደእኔ እምነት አማራጭ ሲጠፋ ሌሎች አገራት በጉዳዩ እንዲገቡ ማድረግ ይቻል ነበር ፤ በአፍሪካ ውስጥ ያለውን ሁሉንም አማራጭ መጠቀም ሳይቻል ወደ ሌላ ማቅናት አሳፋሪ ነው። በዚህ ረገድ ግብፅና ሱዳን ጉዳዩን ወደ ውጭ አካላት ለመውሰድ የሚያደርጉት ጥረት ድርድሩን ለማበላሸት ካላቸው ፅኑ ፍላጎት የተነሳ ነው ብሏል።

እንደ መሃመድ አልአሩሲ ገለጻ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በዲፕሎማሲ ረገድ እያደረገ ያለው ጥረት በጣም የሚደነቅና መላውን ኢትዮጵያውያንን ያኮራ ነው። በተለይም የኢትዮጵያውያንና የአገሪቱን ጥቅም አለማስደፈሩ ትልቅ ከበሬታ ሊሰጠው ይገባል።

ኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳን ዓለምአቀፋዊ ተፅእኖ ለመፍጠር እያደረጉ ያሉትን እንቅስቃሴ በመመከት ረገድ ብዙ ሥራ መሥራት እንደሚያስፈልግ ያመለከተው አቶ መሀመድ፣ በዲፕሎማሲም ሆነ በሚዲያ ዘመቻ በኩል ትልቅ ሥራ ይጠበቅብናል ብሏል። ይህንን ሥራ በተደራጀና በተጠና መንገድ ማከናወን እንደሚገባ አሳስቧል።

‹‹አንዳንዱን ነገር በጣም በጥንቃቄ መመልከትን ፣ ማጥናት፣ አዳዲስ ነገሮች በደንብ መከታተልን የሚጠይቅ ነው ያለው አቶ መሀመድ ፣ ውጤታማ ለመሆን ለዚህ እራስን በአግባቡ ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ አመልክቷል።

እንደ መሀመድ አል አሩሲ ማብራሪያ፤ ግብፅ ያላትን ክብር ኢትዮጵያም በዓለም ሆነ በአፍሪካ ላይ አላት። ሌላው ይቅርና ኢትዮጵያ በአረብ አገራትም ጭምር ትልቅ ክብር፣ታሪክ እና ህዝብ ያላት አገር ናት። በመልካ ምድራዊ አቀማመጧም በአረብ አገራቱ ዘንድ ትልቅ ስፍራ ያላት ናት። በቀደሙት ዓመታት ከአረብ ሀገራት ጋር የነበራት ግንኙነት ትልቅ ክፍተት ነበረው። አብዛኞቹ የአረብ ሀገራት ስለኢትዮጵያ በቂ እውቀት እንዲኖራቸው አልተደረገም።

በተቃራኒው ደግሞ ግብፅ በብቸኝነት የራስዋን አጀንዳ ስታስተላልፍ መኖሯን አስታውሶ፤ በተለይም ባሏት በርካታ ሚዲያዎች ሁሉ በመጠቀም የራሷን ችግር ብቻ ስትገልፅ እንደነበር ጠቁመው ፣ ‹በአንፃሩ በኢትዮጵያ በኩል ዝምታ ነበር ፣ ያ ክፍተት አሁን ላለንበት ችግር መንስኤ ሆኗል ብሏል።

በሀገራቱ መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት በመጠቀም ጉዳዩን በሁለቱም ወገን በኩል እንዲያዩት ማድረግ እንደሚገባ ያመለከተው አቶ መሀመድ ፣ ‹ የግድ እኛ

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.