ወጣቶች በግድቡ ግንባታ ላይ ያለውን ተጽዕኖ በመገንዘብ በዲጅታል ሚዲያው በስፋት እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ቀረበ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ወጣቶች በግድቡ ግንባታ ላይ ያለውን ተጽዕኖ በመገንዘብ በዲጅታል ሚዲያው በስፋት እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ቀረበ

(ኢ ፕ ድ)

ወጣቶች ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ እያሳደረ ያለውን ተጽዕኖ በውል በመረዳት ትክክለኛውን እውነት መረጃን ለዓለም ለማሳወቅ በዲጅታል ሚዲያው በስፋት እንዲንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ወጣቶች የሠላም በጎፈቃደኛ ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ዮሐንስ ጣሰው ጥሪ አቀረቡ።

አቶ ዮሐንስ ጣሰው በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ ዲጅታል ሚዲያው በዓለም ላይ ያለው ኃይልና የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከፍተኛ ነው። ይህን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከግብ እንዳይደርስ እየሠሩ ያሉ ወገኖች ዓለም ለግድቡ ያለው እይታ የተዛባ እንዲሆን እርብርብ እያደረጉ ነው።

ዲጅታል ሚዲያ ቀላል ጊዜ፣ ቀላል ጉልበትና ቀላል ሀብት በመጠቀም ሃሳባችንን ለዓለም ማድረስ የሚያስችል በመሆኑ ወጣቶች ሁሉንም ዓይነት አማራጮች በመጠቀም መሬት ላይ ያለውን እውነትና ትክክለኛውን የአገሪቱ ገጽታ ዓለም እንዲገነዘበው ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸው አመልክተዋል።

የዓባይ ጉዳይ በተለያዩ ዘመናት በነበሩ ወጣቶች ልብ ውስጥ የነበረና በምን መልኩ ተጠቅመን የአገራችንን እድገት እናፋጥን የሚለው እንቆቅልሽ ሳይፈታ ቆይቷል። አሁን ላይ ያሉ ወጣቶች ዕድለኛ ሆነው ሌሎቹ ሲያዜሙለትና ሲቀኙለት ብንሠራው፣ ብንገድበው ይችን አገር ብናሳድግበት የሚለውን ህልማቸውን በቀጥታ ወደ ተግባር ይዞ የገባ ትውልድ አካል መሆን ችለዋል ብለዋል።

ይህን የትውልዶች ሁሉ የዘመናት ህልምና ቁጭት የነበረውን ዓባይ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚደረገውን ሩጫ በፖለቲካና በሌሎችም አጀንዳዎች ምክንያት ሳይዘናጉ ግንባታው ሲጀመር በነበረው ግለት ልክ መደገፍ አስፈላጊ መሆኑንም አመልክተዋል።

በግንባታው እየተሳተፉ ያሉት ባለሙያዎች አብዛኞቹ ወጣቶች መሆናቸውን ያመለከቱት ፕሬዚዳንቱ፤ ዘርፈ ብዙ የሆነውን ተሳትፏቸውን አጠናክረው በመቀጠል በመገባደድ ላይ የሚገኘውን ግድብ ለማጠናቀቅ ዝግጁ መሆን እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

እንደ አቶ ዮሐንስ ገለጻ፤ የኢትጵያ ወጣቶች ስግብግቦች አይደሉም። ከተፋሰሱ አገሮች ወጣቶች ጋር ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ይህን ግድብ ለመጠቀም አያመነቱም። ይህንን የምናረጋግጠው ከተለያዩ የዓለም አገሮች የሚመጡ ወጣቶችን እንዴት አድርገው እንደሚቀበሉ፣ እንዴት አድርገው ተግባብተውና ተዋህደው ውለው እንደሚያድሩ ሲታይ ነው። ስለሆነም ሌሎች አገሮች በግድቡ ግንባታ ምክንያት ጉዳት ይደርስብናል ብለው መስጋት የለባቸውም ብለዋል።

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.