ኢትዮጵያ ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ የሆነ በአባይ ውሃ የመጠቀም መብቷን የሚያቅብ ማናቸውም ዓይነት ስምምነት አትፈርምም - የውሃ፣መሰኖ እና ኢነርጂ ሚንስቴር - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ኢትዮጵያ ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ የሆነ በአባይ ውሃ የመጠቀም መብቷን የሚያቅብ ማናቸውም ዓይነት ስምምነት አትፈርምም - የውሃ፣መሰኖ እና ኢነርጂ ሚንስቴር

በኮንጎ ኪንሻሳ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ስለሚቀጥልበት ሁኔታ ለመመካከር የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ሚኒስትሮች ስብሰባ አውንታዊ ውጤት እንዳይኖረው ግብጽ እና ሱዳን እንቅፋት ሆነዋል ሲል የኢፌዴሪ የውሃ፣መሰኖ እና ኢነርጂ ሚንስቴር አስታወቀ፡፡

በሁለቱ ሀገራት ስምምነት ሳይደረስ ግድቡ መሞላት የለበትም በሚል የሚቀርብ አቋም የህግ መሰረት የሌለው እንዲሁም ኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብቷን የመጠቀም መብቷን የሚጋፋ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብሏል በመግለጫው፡፡

የግድቡ አሞላል እና ተያያዥ የውሃ አለቃቀቅ ላይ የሚደረግ ስርዓት ላይ ለመስማማት ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ዝግጁ ብትሆንም ግብጽ እና ሱዳን በግድቡ ላይ የሚደረገው ድርድር እና ውጤት የኢትዮጵያን የውሃ ድርሻ የሚገድብ እና አለን የሚሉትን የውሃ ክፍፍል የሚያጸና አስገዳጅ ስምምነት ካልተደረገ የሚል ግትር አቋም ይዘዋል፡፡

በስብሰባው ሶስቱ ታዛቢዎች (ደቡብ አፍሪካ፣ አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት) በታዛቢነት እንዲቀጥሉ ሰምምነት የተደረሰ ሲሆን፣ስሊሚኖራቸው ሚና ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ሶስቱ ሀገራት በጋራ ስምምነት ሲጠየቁ ብቻ ሃሳብ ለማቅረብ ለመፍቀድ እትዮጵያ ተስማምታለች፡፡

ግብጽ እና ሱዳን ታዛቢዎቹ ከአፍሪካ ህብረት እኩል ተሳትፎ የማድረግ ሚና ሊሰጣቸው ይገባል በሚል ያቀረቡት ሀሳብ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ ይህ የሁለቱ ሀገራት አካሄድ የአፍሪካ ህብረትን ሚና የሚያሳንስ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ የሆነ የአሁኑ እና የወደፊት በአባይ ውሃ የመጠቀም መብቷን የሚያቅብ ማናቸውም ዓይነት ስምምነት አትፈርምም ነው ያለው ሚንስቴሩ፡፡

በዲሞክራቲክ ሪፕብሊክ ኮንጎ የውጪ ጉዳይ ሚንስትርና የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀመንበር የቀረበውን ረቂቅ መግለጫ ኢትዮጵያ ለመቀበል መስማማቷን ስትገልጽ፣ ግብጽና ስዳን በሁለቱ ቀናት ውይይት ያልተነሱ ጉዳዮች ካልተካተቱ በሚል አንቀበልም በማለት ድርድሩ አውንታዊ ውጤት እንዳይኖረው እንቅፋት ሆነዋል፡፡

የዲሞክራቲክ ሪፕብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሰብሳቢ ፕሬዝደንት ፌሊክስ ሼሲኬዲ እና ቡድናቸው ድርድሩን ለማስቀጠል ያሳዩትን ብርቱ ጥረት የኢትዮጵያ መንግስት በከፍተኛ አክብሮት ይመለከተዋል ብሏል የውሃ፣መሰኖ እና ኢነርጂ ሚንስቴር በመግለጫው፡፡

ኢትዮጵያ የድርድሩ ሒደት የሀገራቱን ሙሉ ባለቤትነት በሚያረጋግጥ እና የአፍሪካን ህብረት የማስተባበር ሚና በተሟላ አኳኋን የሚያስጠብቅ የሶስትዮሽ ድርድር ለመከተል ዝግጁ ናት፡፡

ኤፍ ቢ ሲ

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.