ለግድባችን ስኬትና ለሀገራችን ሉዓላዊነት ከመቼውም ጊዜ በላይ ተባብረን የምንቀሳቀስበት ታሪካዊ ወቅት ላይ እንገኛለን-አቶ ደመቀ መኮንን - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ለግድባችን ስኬትና ለሀገራችን ሉዓላዊነት ከመቼውም ጊዜ በላይ ተባብረን የምንቀሳቀስበት ታሪካዊ ወቅት ላይ እንገኛለን-አቶ ደመቀ መኮንን
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 10ኛ ዓመት በዓልን አስመልክቶ የእንኳን በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸው ሃገራችን የልማት እና ዕድገት ውጥኗን በፍጥነት ለማስቀጠል ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ አቅም መሰረት ከሚጥሉ የመሰረተ ልማት ግንባታ ፕሮጀክቶች መካከል በቀዳሚነት የሚነሳው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት መሆኑን አንስተው ለኢትዮጵያውያን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ከምንም በላይ በቀዳሚነት የሚጠቀስበት ትልቁ ምክንያት ታሪካዊ ትርጉም እና ኢኮኖሚያዊ ፍቺ በመያዙ መሆኑንም ገልፀዋል።
ለዘመናት ያለአንዳች ፋይዳ ሲፈስ የነበረው ታላቁን የአባይ ወንዛችንን ለሃይል ማመንጫነት ሙሉ በሙሉ በራሳችን ሃሳብ፣ ጉልበት እና ገንዘብ ከዛሬ አስር ዓመት በፊት የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጠን አሁን የግንባታውን ሂደት ወደ ማገባደጃ ምዕራፍ መሸጋገራችን ታሪካዊ ትርጉሙን ይበልጥ ከፍ ያደርገዋል።
በተያያዥነት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ የሀገራችንን የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት በከፍተኛ ደረጃ የሚያሻሽለው ከመሆኑ ባሻገር፤ ለታችኛው ተፋሰስ ሃገሮች እና ለቀጠናው ሃገራት በሃይል ልማት ጠንካራ ትስስር መፍጠር ማስቻሉ ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ፍቺ ይይዛል ሲሉም በመልዕክታቸው አስፍረዋል።
ባሳለፍናቸው የግንባታ ዓመታት በፕሮጀክቱ አፈፃፀም ዙሪያ የተስተዋሉ ክፍተቶችን በጥናት በመለየት እና የዕርምት ዕርምጃዎችን በትኩረት በመውሰድ ግንባታው ወደ ማገባደጃ ምዕራፍ ለማሸጋገር ተችሏል ነው ያሉት ።
ለዚህም ከመነሻ ጀምሮ ገንዘባቸውን፣ ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ሃሳባቸውን እና ድምፃቸውን በመስጠት ፕሮጀክቱ ወደ ማገባደጃው ምዕራፍ እንዲሸጋገር ድጋፍ ላደረጉ በሃገር ውስጥ እና በውጭ ለሚኖሩ ወገኖች በብሄራዊ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት እና በራሳቸው ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በዚህ ዓመታት በጠንካራ የሃገር ፍቅር ስሜት የታየው ህዝባዊ ተሳትፎ እና ንቅናቄ ለቀሪ የፕሮጀክቱ ስራ ስኬታማ አፈፃፀም ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.