አቶ ደመቀ መኮንን በህዳሴ ግድብና ተያያዝ ጉዳዮች ላይ በሱዳንና ደቡብ ሱዳን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛን ተቀብለው አነጋገሩ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

አቶ ደመቀ መኮንን በህዳሴ ግድብና ተያያዝ ጉዳዮች ላይ በሱዳንና ደቡብ ሱዳን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛን ተቀብለው አነጋገሩ

አቶ ደመቀ መኮንን በህዳሴ ግድብና ተያያዝ ጉዳዮች ላይ በሱዳንና ደቡብ ሱዳን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛን ተቀብለው አነጋገሩ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሱዳንና ደቡብ ሱዳን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ የተመራ ከፍተኛ ልዑካንን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
አቶ ደመቀ ለልዑካን ቡድኑ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድርና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችን አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ ለአባይ ወንዝ 86 በመቶ ውሃ የሚታበረክት አገር መሆኗዋንና 60 በመቶ የሚሆኑ ዜጎችዋ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ባለማግኘት በጨለማ ውስጥ የሚኖር መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ግድቡ በጨለማ የሚኖር ህዝቧን ብርሃን እንዲያገኝ ለማድረግ የታለመ ፕሮጄክት መሆኑን አስረድተዋል።
የአባይ ውሃን በፍትሃዊና እኩልነት መርህ ለልማት ማዋል የኢትዮጵያ ህጋዊና ሉዓላዊ መብት መሆኑን አስረድተው፣ ኢትዮጵያ ታችኞቹን የአባይ ተፋሰስ አገራትን የመጉዳትምንም ፍላጎት እንደሌላት አቶ ደመቀ ለቡድኑ ገልፀውላቸዋል።
በሱዳንና በግብጽ በኩል የሚነሱ ስጋቶች ለመፍታት የሶስትዮሽ ድርድር ሲካሄድ መቆየቱን በማስታወስ፤ የሚነሱ ጉዳዮች በድርድር መፍትሔ ያገኝ ዘንድ ኢትዮጵያ ያላትን አቋም አብራርተዋል፡፡
በአፍሪካ ህብረት በዲሞክራቲክ ኮንጎ መሪነት የሚካሄደው ድርደር እንዲቀጥል የኢትዮጵ ፍላጎት መሆኑን ጠቅሰው፣
የሶስትዮሽ ሂደት መለወጥ ካስፈለገም ሶስቱ አገራት እ.ኤ.አ በ2015 የተፈራረሙት የመርሆዎች መግለጫ ስምምነት(DOP) መሰረት መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
የግድቡ ደህነት አስመልክቶ ሱዳን የጠየቀቻቸው መረጃዎችንም የተሰጣት መሆኑን ገልጸው፣ ኢትዮጵያ ለጉዳዮ በድርድር እንዲፈታ ቁርጠኛ መሆንዋን ለልዑካኑ ገልፀዋል።
በግድቡ የውሃ ሙሌት የግንባታው አንድ አካል መሆኑን ጠቅሰው፤ እንደ አሜሪካ ያሉ ወዳጅ አገሮች የህዳሴ ድርድር እንዲሳካና በአከባቢው ያሉ አገሮች መካከል ያለው ግንኙነት እንዳይሻክር ለሚያደርጉት ጥረት ምሰጋና አቅርበዋል። ከአሜሪካ ጋር በትብበር ለመሥራት ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን አቶ ደመቀ አረጋግጠዋል፡
******************
(ኢ ፕ ድ)

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.