በህዳሴ ግድብ ዙሪያ አራተኛ አደራዳሪ አካል እንዲገባ የሚቀርበው ጥያቄ ትርጉም የለሽ ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

በህዳሴ ግድብ ዙሪያ አራተኛ አደራዳሪ አካል እንዲገባ የሚቀርበው ጥያቄ ትርጉም የለሽ ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
በህዳሴ ግድብ ዙሪያ አራተኛ አደራዳሪ አካል እንዲገባ የሚቀርበው ጥያቄ ትርጉም የለሽ ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሶስትዮሽ ድርድሩ ባልተቋጨበት አራተኛ አደራዳሪ አካል እንዲገባ የሚቀርበው ጥያቄ ትርጉም የለሽ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ህብረት መራሹ የሶስትዮሽ ድርድር አክብሮት አላት ብለዋል ።
አሁን ላይ የሶስትዮሽ ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የስልጣን ሽግግር ምክንያት ለጊዜው መቋረጡንም ጠቅሰዋል ።
የህብረቱን ሊቀመንበርነት ከደቡብ አፍሪካ የተቀበለችው ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሶስቱንም ሀገራት በድርድሩ ዙሪያ በተናጠል ማናገሯን ገልጸዋል ።
አሁን ያለው ድርድር ውጤታማ መሆን አለመሆኑ ሳይታወቅ ሌላ ድርድር መጥራት ተገቢነት እንደሌለውም ቃል አቀባዩ ገልጸዋል ።
ድርድሩ ውጤታማ ባይሆን እንኳ የሚመራው በፈረንጆቹ 2015 በመሪዎች ደረጃ በተደረሰው የመርሆዎች ስምምነት በተቀመጠው መንገድ ይሆናልም ብለዋል ቃል አቀባዩ፡፡
በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን መልዕክተኛ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንዲሁም ከሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ጋር መወያየታቸውን አውስተዋል።
በውይይቱ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት ስላካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ እና ሰብዓዊ ድጋፍ ገለጻ መደረጉን አስረድተዋል።
በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ በርካታ የረድኤት ድርጅቶች ጥያቄ ማቅረባቸውን ያነሱት ቃል አቀባዩ፥ ድርጅቶቹ ወደ ተግባር ሲገቡ ግን ባቀረቡት ጥያቄ ልክ አለመሆኑን ጠቁመዋል፡፡
አሁን በረድኤት ድርጅቶች እየቀረበ ያለው ድጋፍ ከ30 በመቶ የበለጠ አለመሆኑን እና 70 በመቶው እየቀረበ ያለው በመንግሥት በኩል መሆኑንም አስታውሰዋል።
በዓላዛር ታደለ

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.