ኘሬስ ሪሊዝ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ም/ቤት ጽ/ቤት - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ኘሬስ ሪሊዝ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ም/ቤት ጽ/ቤት
ኘሬስ ሪሊዝ
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ም/ቤት ጽ/ቤት
- መጋቢት 1ዐ/ 2ዐ13 ዓ.ም.
- እንደደረሰ ጥቅም ላይ የሚውል
- የ2ዐ13 የቦንድ ሳምንትን አስመልክቶ የተጻፈ
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የቦንድ ሳምንት ሊጀመር ነው፡፡
ታላቁ ህዳሴ ግድብ ከተበሰረበት ዕለት መጋቢት 24/2ዐ13 ዓ.ም. ጀምሮ መላው ኢትዮጵያውያን ከጫፍ ጫፍ በመነሳት በሞራልና በገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ሲሆኑ ባለፉት 1ዐ ዓመታት 14.98 ቢሊዮን ብር ከህዝባችን ለግድቡ ድጋፍ ተደርጓል፡፡ ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪ ለግድቡ አምባሳደር በመሆን በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በፍትሃዊ የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ግድቡን እየገነባን መሆኑን እንዲገነዘብ እና የሶስተኛ ወገን ጣልቃ-ገብነት አድሎአዊ ውሳኔ እንዲቀለበስ ሰፊ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ስራ ሰርተዋል፡፡ በዚህም የሀገራችንን ገጽታ ከመገንባት በተጨማሪ በተፈጥሮ ሃብታችን የመጠቀም ሉዓላዊ መብታችንን በማረጋገጥ 10 ዓመታትን በአንድነት በድል የታጀበ ጉዞ አድርገን ግድቡንም 79 በመቶ በማድረስ በማገባደድ ላይ እንገኛለን፡፡
ኢትዮጵያውያን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የጀመርነው ድጋፍ ላለፉት አስር ዓመታት ላፍታም ያልተቋረጠ ሲሆን ህብረተሰቡ የታላቁ ህዳሴ ግድብን ቦንድ እየገዛ ባንድ በኩል ግድቡን እየገነባ በሌላ በኩል የቁጠባ ባህሉን በማሳደግ ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክና የኢትዮጰያ ንግድ ባንክ በያመቱ የግድቡ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠበትን ዕለት በማስመልከት በመላው ሃገሪቱ የቦንድ ሽያጭ ሳምንት እያዘጋጁ የነበረ ሲሆን በዘንድሮም ከመጋቢት15 እስከ መጋቢት 25/2013ዓ.ም. ለ1ዐ ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የቦንድ ሳምንት በመላው ሃገሪቱ ይካሄዳል፡፡ ይህ የቦንድ ሳምንት መጋቢት 14/2013 በኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ሰዓት የተለያዩ አካላት በሚገኙበት በይፋ ይበሰራል፡፡
በመሆኑም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ በዚህ የቦንድ ሳምንት በነቂስ በመሳተፍ ከ5ዐ ብር እና 1ዐዐ ብር ጀምሮ አቅማችሁ በፈቀደ መጠን ለራሳችሁ፣ ለልጆቻችሁ እንዲሁም ለምትወዷቸው ሰዎች ጭምር የቦንድ ግዥ በመፈፀምና በስጦታ በማበርከት የአንድነታችን እና ሉዓላዊነታችን መገለጫ የሆነውን የታላቁ ህዳሴ ግድባችንን 1ዐኛ ዓመት ታከብሩ ዘንድ ጥሪያችንን እያቀረብን፡፡ የሁላችንም አሻራ ላረፈበት እና የልጆቻችን ተስፋ ለሆነው ለታላቁ ህዳሴ ግድብ 1ዐኛ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ እንላለን! መልካም የ10ኛ ዓመት በዓል ይሁንላችሁ! ይሁንልን!
# # #

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.