“የህዳሴ ግድብ እንዲጠናቀቅ ሕዝቡ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ ነው” -ዶክተር አረጋዊ በርሄ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ጽህፈት ቤት ዋና - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

“የህዳሴ ግድብ እንዲጠናቀቅ ሕዝቡ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ ነው” -ዶክተር አረጋዊ በርሄ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ጽህፈት ቤት ዋና

“የህዳሴ ግድብ እንዲጠናቀቅ ሕዝቡ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ ነው” -ዶክተር አረጋዊ በርሄ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ጽህፈት ቤት ዋና
መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሠራቸው የልማት ሥራዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰውን የህዳሴ ግድብ እንዲጠናቀቅ ህዝቡ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ ገለፁ።
ዶክተር አረጋዊ በርሄ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቅት፣ የህዳሴው ግድብ የአገሪቱ ተስፋ መሆኑን ከህፃን እስከ አዋቂ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ስላመነበት አሁን ላይ ሥራው እንዲጠናቀቅ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል።
ሕዝቡ በጉልበቱ፣ በእውቀቱ እና ባለው ሁሉ የግድቡን ሥራ እያገዘ እንደሆነ ያመለከቱት ዶክተር አረጋዊ፣ በመንግሥት በኩል የሚደረጉ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችንም በትኩረት እየተከታተለ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ በነበሩባት የውስጥ የቤት ሥራዎቿ ምክንያት እስከ ዛሬ ድረስ በገንዛ ውሃዋ ሳትጠቀም ቆይታለች ያሉት ዶክተር አረጋዊ፣ አሁን ደግሞ ጊዜው ደርሶ አልምታ ለመጠቀም እየሠራች ነው። በዚህ ሀብቷ አትጠቀሚ ማለት ከፍተኛ ስህተት ከመሆኑም በላይ የቀኝ ግዛት ሥነ ልቦና የፈጠረው ችግር መሆኑን አመልክተዋል።
ሱዳንና ግብጽ አሁን እያነሱ ያለው አጀንዳ መሰረታዊ አይደለም የሚሉት ዶክተር አረጋዊ፣ ምክንያቱም ለብዙ ዘመናት ውሃውን ብቻ ሳይሆን አፈራችንንም በአግባቡ ተጠቅመውበታል፤ አሁን ደግሞ ጊዜው በጋራ የመልማት ነው ብለዋል።
ሱዳንና ግብጽ ሥር ሥር እየሄዱ የግድቡን ግንባታ ለማደናቀፍ የሚፈጥሯቸው ምክንያቶችና ችግሮች የኢትዮጵያ ሕዝብ ለግድቡ ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጥ ከማድረጉም በላይ ቁጣንም ያጫረ መሆኑንም አመልክተዋል።
ሕዝቡ ከዚህ በፊትም ቢሆን በዓባይ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ የሆነ ቁጭት ነበረበት ወደ ተግባር ያልገባውም የሚያደራጀው አካል ባለማግኘቱ ነው፤ በመሆኑም የግድቡ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ይህንን ህዝብን የማደራጀት ሥራ እየሠራ ይገኛል ብለዋል።
እስከ አሁን ባለው ሁኔታም ህዝቡ በግድቡ ላይ የኔነት ስሜት እንዲሰማው በማድረግ ብሎም ያለውን በመስጠት ተሳትፎውን እያሳየ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ በቅርቡ እንኳን በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ሰባት መቶ ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ መቻሉን ጠቁመው፣ ባለፉት ስድስት ወራትም አንድ ነጥብ ስደስት ቢሊየን ብር ከመላው አገሪቱ ለመሰብሰብ ተችሏል ብለዋል። ይህ የሚያሳየው ደግሞ ህዝቡ አሁንም በግድቡ ግንባታ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ መነቃቃት ውስጥ መሆኑን እንደሆነ አመልክተዋል።
ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ ህዝቡን ከማስተባበር ባሻገር በዲፕሎማሲው እና፣ በፖለቲካው መስክ ተሳትፎው እያደረገና ሥራዎችን እየሠራ ነው። በተለይም ዲያስፖራው የራሱን ተሳትፎ ከማድረግ ባሻገር ሌሎች የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆኑ የውጭ አገር ዜጎችን በማስተባበር እንዲሰራ የበኩሉን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የግድቡ መሰረት ድንጋይ የተጣለበት 10ኛ ዓመት እንደመሆኑ ጽህፈት ቤቱ በርካታ የንቅናቄ ሥራዎችን ለመሥራት አቅዷል ያሉት ዶክተር አረጋዊ፣ ይህንንም በተግባር ለማዋል ከመገናኛ ብዙሃን፣ ከአርቲስቶች፣ ከወጣቶችና ከሌሎችም ጋር በመሆን የነቅናቄ ሥራውን ለመሥራትና ለግድቡ መጠናቀቅም ትልቅ አስተዋጽኦ ለማበርከት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አመልክተዋል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 8 ቀን 2013 ዓ.ም

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.