በመተከል ተከስቶ የነበረው የጸጥታ ችግር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስጋት አይሆንም - የመተከል የተቀናጀ ግብረ ሃይል - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

በመተከል ተከስቶ የነበረው የጸጥታ ችግር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስጋት አይሆንም - የመተከል የተቀናጀ ግብረ ሃይል

በመተከል ተከስቶ የነበረው የጸጥታ ችግር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስጋት አይሆንም - የመተከል የተቀናጀ ግብረ ሃይል
አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ተከስቶ የነበረው የጸጥታ ችግር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስጋት እንደማይሆን የዞኑ የተቀናጀ ግብረ -ሃይል አስታወቀ።
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በማንኛውም ጊዜ ማድረስ የሚያስችል አስተማማኝ የጸጥታ አደረጃጀት እንዳለም አረጋግጧል።
በመተከል ቡለንና ድባጤ ወረዳዎች የሽፍታው ቡድን አባላት በንጹሃን ላይ ባደረሱት ግድያና መፈናቀል በዞኑ የጸጥታ ስጋት ተፈጥሮ እንደነበረ ይታወሳል።
የጸጥታ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትና ዞኑን ወደነበረበት ሰላም ለመመለስ በፌዴራል መንግስት የተዋቀረው ግብረ-ሃይል የጸጥታና ህግ ማስከበር ስራውን እንዲረከብ ተደርጓል።
በዚህም ግጭት የተከሰተባቸውን ጨምሮ ግጭት ሊከሰትባቸው ይችላል በተባሉ ቦታዎች አንፃራዊ ሰላም መስፈን ችሏል ነው የተባለው።
ግብረ-ሃይሉም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሌሎች የዞኑ ወረዳዎችን በመመልከት ከግድቡ ሰራተኞችና ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት አድርጓል።
የመተከልን የተቀናጀ ግብረ ሃይል የሚመሩት ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ እና ሌሎች የግብረ ሃይሉ አባላት ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጎብኝተዋል።
ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የግድቡ ግንባታ ሲጀመር ጀምሮ ጸጥታውን ታሳቢ ያደረገ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባላት አደረጃጀት ተፈጥሯል።
በመሆኑም በውስጥም ሆነ በድንበር ያሉ ጉዳዮች በትኩረት ክትትል እየተደረገባቸው በመሆኑ ስጋት አይኖርም ብለዋል።
የአገር መከላከያ ሰራዊት ከግድቡ ሰራተኞችና አመራሮች ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን የገለጹት ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ፤ ሃላፊነት በጎደላቸው ማህበራዊ ድረ- ገፆች የሚተላለፉት የተሳሳቱ መረጃዎች የመተከልን ነባራዊ ሁኔታ አይገልጹም ብለዋል።
ከዚህም ባሻገር ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል ግብዓት በማንኛውም ሰዓት ለመቅረብ የጸጥታ ስጋት የሌለበት የትራንስፖርት አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንም አስታውቀዋል።

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.