የጆ ባይደን አስተዳደር በህዳሴ ግድብ ላይ ጣልቃ እንደማይገባ ተስፋ አደርጋለሁ- አምባሳደር አለማየሁ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የጆ ባይደን አስተዳደር በህዳሴ ግድብ ላይ ጣልቃ እንደማይገባ ተስፋ አደርጋለሁ- አምባሳደር አለማየሁ

የጆ ባይደን አስተዳደር በህዳሴ ግድብ ላይ ጣልቃ እንደማይገባ ተስፋ አደርጋለሁ- አምባሳደር አለማየሁ
አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ አዲሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳዳር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ዙሪያ የቀድሞው መንግስት እንዳደረገው በጉዳዩ ላይ እጁን እንደማይጭን ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ገለፁ።
አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ “ስፑትኒክ አረቢክ” ከተሰኘው መገናኛ ብዙሃን ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል።
በሩሲያ ፌዴሬሽን የኢፌ.ዲ.ሪ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ለመገናኛ ብዙሃን በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ፣ ከሱዳን ጋር ስላለው ወቅታዊ የድንበር ጉዳይ፣ በሩሲያ ስለቀረበው የኮቪድ 19 ክትባት እና በሩሲያና በኢትዮጵያ መካከል ስላለው ትብብር ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶም በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የሚመራው አዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ዙሪያ የቀድሞው መንግስት እንዳደረገው በጉዳዩ ላይ እጁን እንደማይጭን ተስፋ አደርጋለሁ በማለት መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያሉትን ሁሉንም ጉዳዮች በአፍሪካ ተቋማት በኩል መፍታት እንደሚቻል ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታምንና ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከጉዳዩ አንጻር ገለልተኛነት እንደምትጠብቅ አስረድተዋል ፡፡
ከሱዳን ጋር ስላለው ወቅታዊ የድንበር ጉዳይ ለቀረበላቸው ጥያቄም መልስ የሰጡት አምባሳደሩ የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን ከማንኛውም ወታደራዊ አማራጭ ይልቅ ውይይት እና ሰላማዊ መፍትሄን የመረጠ መሆኑን ገልፀዋል።
ሁለቱ ሀገራት ከድንበር ውዝግብ ባሻገር ብዙ የሚጋሯቸው ጉዳዮችና ጠንካራ የህዝብ ለህዝብ ወዳጅነት ያላቸው መሆኑንና የሰላም መንገድ ለመምረጥ ከሱዳን በኩል ፍላጎት ካለ በፍጥነት ጉዳዩን በተቻለ ፍጥነት በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡
ስፑትኒክ ስለተሰኘውና የሩሲያ ምርት ስለሆነው የኮሮና ቫይረስ ክትባት በተመለከተም ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከል ብሎም ለማጥፋት ኢትዮጵያ በዓለም ዓቀፉ ህብረተሰብ የሚደረገው ዘመቻ አካል እንደመሆንዋ መጠን የኢትዮጵያ ህግ በሚፈቅደው መንገድ ስምምነት በማድረግ ክትባቱ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባበት መንገድ ቢመቻች ፍላጐት መኖሩን ገልፀዋል፡፡

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.