የአባይ ውሃ የትውልድ ህይወት ነው - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የአባይ ውሃ የትውልድ ህይወት ነው

ውሃ ሕይወት፣ ውሃ ስልጣኔ፣ ውሃ ሀብት ወዘተ…. ነው፡፡ ምድራችን ያለውሃ የሕያዋን መኖሪ መሆን ባልቻለች ነበር፡፡ በዓለማችን ላይ ቀዳሚ ስልጣኔዎች በውሃ ዳር ተጀመሩ ሲባል መስማት ብቻ ሣይሆን፤ ዛሬ በዓለም ላይ ግዙፎቹ ከተሞች… መንደሮች ወዘተ ተገንብተው አብበው የሚታዩት በውሃዎችና በወንዞች ዳር ነው፡፡ ውሃ ሕይወት ነው ብንልም የአባይ ውሃ የበለጠ ሕይወት ነው፡፡
በኛው ሀገር በሁሉ ነገር ለማደግ ዕድልና ተስፋ አላቸው የሚባት ውሃ ዳር የተገነቡ ከተሞች እንደ ባህርዳርና ሀዋሳ ያሉ ናቸው፡፡ ከውሃ ዳር ርቀው የተገነቡ ከተሞቻችን የዕድገት ተስፋቸው በእጅጉ አናሣና አሳሳቢ ከመሆኑም ውሃ ያግኙ ሲባል ሀብታችንን አሟጠው ይበሉብናል፡፡ ወይም እየበሉን ነው፡፡
ከወንዞቻችን ሁሉ ታላቁን ያሉንን አብዛኞቹን ወንዞች በግራቪቲ ኃይል አስተባብሮና አስገብሮ አፈራችንን ጠራርጎ ለባዕድ ይዞ የሚጓዘው አባይ የስልጣኔያችን መነሻ ከመሆኑም እንጠቀምብህ ስንለው የሚያመጣብን መዘዝ ጎልቶ መታየቱና ቀርቦ መምጣቱ ከምን ጊዜም በላይ እኛን ኢትዮጵያውያንን በጥብቅ ዲሲፒሊን በጋራ እንድንቆም ሁኔታው በግልፅ ያስገድደናል ግን ታዲያ እኮ! አባይንና ኃላፊውን ትውልዳችንን የምንወቅሳቸው አባይ ዕድሜውን ሙሉ ከሀገራችን መንጭቶ በባዕድ ሀገር የሥልጣኔ ምንጭ ነው ሲባል መስማቱ፣ ዛሬም ቆሞ ማየቱ ያንገበግባል እልክ ያስይዛል ለመፍትሄው ኢትዮጵያዊን ሁሉ አብረን ጠንክረን እንድንቆም የሕልውና ጉዳያችን ሆኖ ያስገድደናል፡፡ እኛ የዛሬውን የወደፊቱ ትውልዶች አባይ እንደልማዱ ውሃና አፈራችንን ይዞ ሲነጉድ ዝም ብንል፤ በህብረት ቆመን በገንዘባችን የግድቡ ግንባታ እንደጀመርነው ጥርሣችንን ነክሰን በግንባታና በዲፕሎማሲው ትግል ዳር አድርሰን ኤሌክትሪክ ባናመነጭ፣ ካለፉት ትውልዶች ይልቅ በታሪክ ፊት እኛ የዛሬዎቹ ትውልዶች ይበልጥ ተወቃሾች ነን፡፡
ውድ ወገኖቼ!! የአድዋን ድል ከሦስት ቀናት በፊት አከበርን፡፡ የአባቶቻችን ህብረት እስከሞት ድረስ በአንድነት ተነባብረው በመዋጋታቸው፤ ህይወታቸውን ሰጥተው በማሸነፋቸው በታላቅ ስሜት ለማክበር በቃን የጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የነፃነትና የድል መነሻ አደረግነው፡፡ እኛስ የዛሬዎቹ ትውልዶች በሠላማዊ ዲፕሎማሲ ውጊያ የህዳሴ ግድብን ግንባታ ከፍፃሜ አድርሰን ድሉን የምናከብረው መቼ ነው!!?
ተራኪዎች ወይም ታሪክ ፀሐፊዎች እንደሚያቀርቡልን “የአባይ ጉዳይ ለግብፆች በውን ብቻ ሣይሆን በሕልምም ጭምር ያቃዣቸዋል፣ ባንድነት ያቆማቸዋል ምክንያቱም አባይ ሕይወታችን ነው” ይላሉ፡፡ አባይ ወንዝና የህዳሴ ግድብ ለኛ ለኢትዮጵያዊያንም ሀብታችንና ሕይወታችን መሆኑን ተረድተው ተባብረን በጋራ እንቃመሰው እንጠቀምበት ማለቱ ምን ያስከፋል? አንዳንድ የግብፅ ሰዎችም መፍትሄው ውጊያ ነው ሲሉ ይደመጣሉ “የማን ቤት ጠፍቶ የማን ሊበጅ፣ ያውሬ መውለጃ ይሆናል እንጂ!!” የሚለውን የቁርጥ ቀን መፈክራችንን እና ታላቁን የአድዋ ድላችንን አልሰሙም፣ አያውቁም፣ አልተረዱም፣ ይሆን? በዚህ በዘመናዊና በቴክኖሊጂ ዘመን ይፎከራል!!፡፡
ለነገሩ እኮ ግብፆች በአባይ ምክንያት በግብፅም ሆነ በስውር ትግል ከጀመሩን ጊዜው ረዥም ነው
- ከሺ ዓመታት በላይ ጳጳሳት ሊልኩልን የሚቀበሉን ኪሎ ወርቅ አንሷቸው ጳጳሳቶቹን የውሃ አጀንዳ አሸክመው መላካቸው ታላላቅ የሃይማኖት አባቶቻችን ይመሰክራሉሉ፡ ለሺ አምስት መቶ አመታት ያህል የተላኩል 113 ጳጳሣት ውሃ ዳር እንዳንኖር “ያለጊጊ ውሃ ዳር አትሂዱ! ውሃ ውስጥ ሠይጣን አለና ራቁ! መኖሪያና የአምልኮ ቦታ ከውሃ ርቃችሁ ተራራ ላይ ስሩ!” ብለው በቀናውና የዋህ አማኝ ህዝባችን ንቃተ-ሕሊና ላይ መቀለዳቸው የተረካል፡፡
- የታሪክና የዲፕሎማሲ መዛግብት እንደሚመሠክሩት ግብፆች ከሀገር አፍራሾች፣ ከባንጣዮችና ከባንዳዎች ጀርባ ቆመው ወይም በመሆን ወግተውናል፡፡ አስወግተውናል መዘዙ ያው አባይ ወንዝ ነው፡፡ እኛና ግብፆ ተባብረን አባይን ባለመጠቀማችን ግንኙነታችንን የአንቲ-ማተር ያህል ተጠፋፊ አስመስሎናል፡፡
- ግብፆች በዲፕሎማሲው ሂደት የውሃ ሰላዮች በመመደብ፤ ኢትዮጵያን ከሚያጠቁ ሁሉ ጀርባ በመሆን የዲፕሎማሲና የጦር መሣሪያ ድጋፍ ማቀበላቸው የዓለም አቀፍ ግንኙነታቸው መጀመሪያና መጨረሻቸው መሆኑ የአደባባይ ሚስጢር ያህል ነው፡፡
- ግብፆች በውሃችንና በግድባችን በክፋት ከሚመጡብን፤ ለሁላችንም በሚበጅ ሥርዓት በአባይ ገበቴ (Basin) በጋራ ደን ተክለን በማሳደግ የውሀውን ቀጣይነትና መትረፍረፍ በማረጋገጥ የጋራ ተጠቀሚነታችንን ብናዳብርስ? ይህ ቢሆን ለደባ ዲፕሎማሲያቸው ከሚያወጡት ገንዘብ እጅግ ባነሰ ወጪ ውሃውን በማትረፍረፍ እንደ ፍላጎታቸው ሱዌዝን በማሻገር ሸጠን ገንዘቡን በቅንነት መከፋፈል አይቻልም ለነገሩ ግብፆች ዛሬ የሚከራከሩን ውሃችን ከተፈጥሮ ጎዳናው አውጥተው ሸጠው ለመጠቀም ብልጠት ውስጥ መሆናቸውን አንርሣ!! ኢትዮጵያን ያለስርዓት የሚወነጅሉትና የሚገዳደሩን ለዚሁ ድብቅ አጀንዳቸው ነው፡፡ በድርድሩ ሊረቱ ሲሉ፣ ለዲፕሎማሲ ጅል ለሆነው የኃይል ሀገር ፕሬዝዳንት አቤቱታ አቅርበው ለውሃ ነክ ሙያ ማይም በሆኑ አደራዳሪዎች ወቀሳ መደርደሩ ምን ይባላል ታዲያ እኛስ ውሃችን በእጃችን ሆኖ ከግብፆ በላይ መስራት ምን አገደን? ምንስ በውሃችን ያለማምጠናል? በመላው ዓለም የተመደቡ ዲፕሎማቶቻችንና ዲያስፖራውስ የዲፕሎማሲ ሙያቸውንና የቋንቋ ብቃታቸውን የሀገርና የሕዝብ ፍቅር ስሜታቸውን ብቃት የሚጠቀሙት ለመቼ ነው የአፍሪካን ህብረት፤ የአፍሪካን ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከታላላቅ ዲፖሎማቶች ጋር ተደራድረው አሸንፈው አዲስ አበባ ውስጥ በመመሥረት የሀገራችንን ዋና ከተማ ታላቋ የዲፕሎማሲ ማዕከል ያደረጉት የቀደምት ዲፕሎማቶቻችን መንፈስ እንዳይወቅሳቸው የዛሬው ዲፕሎማቶቻችን ሊጠናቀቁና ሊተገበሩ ይገባል፡፡
ክቡራን ተሰብሳቢዎች፤ ግድባችን ዳር ደርሶ ጥቅም ላይ ለማዋል እጅግ ሰፊ ውስጣዊና ውጫዊ ጥንካሬ ከመሪዎችችን፤ ከዲፕሎማቶቻችን፤ በአጠቃላይ ከሕዝባችን ይጠበቃል፡፡ ግድቡ የመላው ሕዝብ አንጡራ ሀብት ስለሆነ መዋጮው ለአንዲት ደቂቃ መዘንጋት ዌም መቋረጥ የለበትም ዋናዎቹ ሚዲያዎችም ሆኑ ማህበራዊ ሚዲያዎች በዚህ ጉዳ መተኛትና ማንቀላፋት የለባቸውም፡፡
በ50ዎቹ መጀመሪ ለግርማዊ ጃንሆይ በአዋቂዎች መልካም ምክር ተሰጥሮ ነበር ይባላል ምክሮቹም “ሀገርዎ ካለችበት ጂኦ-ፖለቲካዊ አኳያ ተፈጥሮአዊና ታሪካዊ ባላንጣ አለብዎት እረፍት አይሰጡዎትም ለዚህ መፍትሄው ዲሞክራሲን ማስፈን፤ ጠንካራ ፕሮፌሽናል ወታደር መገንባት፤ ዘላቂ ልማት ጠንካራ ኢኮኖሚ በአስቸኳ መገንባት ይጠበቅብዎታል” ተብለው ነበር፡፡ በእርጅና ይሁን በሌላ ምክንያታዊ ባልሆነ ዘዴ የቀረበላቸውን መልካም ምክረ-ሃሣብ ተቀብለው ተግባራዊ ሳያደርጉ በመዘግየታቸው መንግስታቸው ጭምር ለውድቀት በቅቷል፡፡
በአባይ ላይ እንኳን ታላቅ ግድብ ሠርተን ይቅርና ትናንሽ ገባር ወንዞች ሳንገነባ የግብፆ ጩኸት እና የዲፕሎማቶቻቸው ሩጫ ዓለምን ያዳርሳል፡፡ ከሃይማኖት እስከ ዘርና ቀለም ጠቅሰው በመከራከር “በአባይ ምክንያት ዲኖሳይድ ሊካሄድብን ነው” እስከ ማለት ይደርሳሉ ይባላል እኛ ኢትየጵያውያን አባይንና ሌሎ ወንዞቻችንን ሳንጠቀም እድጅ ብዙ ዘመናት አልፏል አሁን ንቁ ሆነን በአንድነት ቆመን፣ እጅ ለእጅ ተያይዘን ለትውልድ ተሸጋሪ ሀብት ማኖር ይጠበቅብናል፡፡ ተደራዳሪዎቻችንና መንግስታችን በዚህ አስቸጋሪ የዲፕሎማሲ ሁካታ ወቅት የወሰዳችሁትን እርምጃ አደንቃለሁ ግብፆች ከገባቸው መፍትሄ ዲፕሎማሲያዊ ድርድር ብቻ ነው እንደጀማሪው ጠ/ሚር መለስ ንግግር “ግድባችንን የሚያቆም የለም” እላለሁ፡፡ ግድባችንም ዋጋው ከተመን በላይ ሀብትነቱም የትውልደ ትውልድ ነው እላለሁ አመሰግናለሁ፡፡
አሰፋ ሀብተወልደ

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.