ታላቁ የሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሰየሟቸው ባለሙያዎች ያቀረቡት ረቂቅ ሰነድን ኢትዮጵያ እና ሱዳን ሲቀበሉት ግብፅ ሳትቀበለው ቀርታለች - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ታላቁ የሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሰየሟቸው ባለሙያዎች ያቀረቡት ረቂቅ ሰነድን ኢትዮጵያ እና ሱዳን ሲቀበሉት ግብፅ ሳትቀበለው ቀርታለች

ታላቁ የሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሰየሟቸው ባለሙያዎች ያቀረቡት ረቂቅ ሰነድን ኢትዮጵያ እና ሱዳን ሲቀበሉት ግብፅ ሳትቀበለው ቀርታለች
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2013(ኤፍ.ቢ.ሲ)ታላቁ የሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሰየሟቸው ባለሙያዎች ያቀረቡት ረቂቅ ሰነድን ኢትዮጵያ እና ሱዳን ሲቀበሉት ግብፅ ሰነዱን ሳትቀበለው ቀርታለች ።
በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ዛሬ የተካሄደውን የሶስትዮሽ ውይይት አስመልክቶ የውሃ ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር መግለጫ አውጥቷል።
የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።
አዲስ አበባ (ታሕሳስ 25 ቀን 2013)
የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዛሬው ዕለት በበይነመረብ ስብሰባ አካሂደዋል።
ስብሰባው በደቡብ አፍሪካ የዓለምአቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚ ምከር ቤት ሊቀመንበር ሰብሳቢነት ተካሂዷል።
ሚኒስትሮቹ የሕዳሴው ግድብ ድርድር በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ምክከር ያደረጉ ሲሆን የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሰየሟቸው ባለሙያዎች ያቀረቡት ረቂቅ ሰነድ ላይ በማተኮር ምክክርተደርጓል፡፡
በዚህ መሰረት ኢትዮጵያ ባለሙያዎቹ የቀረጹትን ሰነድ በበጎ እንደምትመለከተው እና በቀጣይ በሚካሄደው ድርድር ሰነዱን እንደግብዓት ለመጠቀም ፈቃደኛ መሆኗን ገልጻለች፡፡
የሱዳንወገን በበኩሉ ሰነዱን ለሂደቱ ጠቃሚ አድርጎ እንደሚመለከተው እና በቀጣይ የአፍሪካ ህብረት ባለሙያዎች ተጨማሪ ሚና ላይ ቢጋር በማጽደቅ ድርድሩን መቀጠል እንደሚፈልግ ገልጿል፡፡
የግብጽ ወገን ሰነዱን ጨርሶ እንደማይቀበለው ገልጿል፡፡
የሕዳሴው ግድብ ሙሌት እና ዓመታዊ ኣስተዳደርን የሚመለከተው ሰነድ ላይ የሚደረገው ድርድር በአመዛኙ መግባባት የተደረሰበት ቢሆንም፣ ወደፊት በዓባይ ተፋሰስ ላይ በሚገነቡ የውሃ ልማት
ሥራዎች ጋር የሚኖረው ቁርኝት ዋነኛ የልዩነት ሃሳብ ነው፡፡
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ፍጆታ የሌለው የኃይል ማመንጫ ግድብ እንደመሆኑ በግድቡ ላይ የሚደረሰው ስምምነት ይህንኑ ከግምት ያስገባ እና የተሟላ የውሃ ስምምነት በሌለበት እና ኢፍትሃዊ አጠቃቀም በሰፈነበት ተፋሰስ የኢትዮጵያን የመጠቀም መብት የሚያቅብ እንዲሆን
ኢትዮጵያ አትፈቅድም::
ይህን መሰረት በማድረግ፣ ኢትዮጵያ የሕዳሴውን ግድብ እሞላል እና ዓመታዊ አስተደዳር የሚመለከተውን ደንብ በጋራ ስምምነት ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ ናት፡፡
በዚህም መሰረት የስምምነት አማራጮችን ለግብጽ እና ሱዳን ወገን ያቀረበች ሲሆን የሃገራቱ ምላሽ ቀና እንደሚሆን ተስፋ
ይደረጋል፡፡
በቀጣይ የሃገራቱ ባለሙያዎች በውሃ ሚኒስትሮች አመራር ስር ስብሰባቸውን በመቀጠል ስምምነት የተደረሰባቸውን እና የልዩነት ሃሳቦችን በመለየት በቀጣይ ዕሁድ ጥር 01 ቀን 2013 ለሚካሄደው
የስድስት ሚኒስትሮች ስብሰባ ውጤቱን ያቀርባሉ፡፡

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.