ግብጽ እና የሙጥኝ ያለችው የቅኝ ግዛት ውል - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ግብጽ እና የሙጥኝ ያለችው የቅኝ ግዛት ውል

የግብጽ መገናኛ ብዙሀን ፣ባለጠጎችና ምሁራን ከሰሞኑ  የጦርነት ነጋሪት በመጎሰም ላይ ተጠምደው ሰንብተዋል፡፡ግብጽ በአንድ በኩል በሶስትዮሽ ድርድር እየተሳተፈች በሌላ በኩል ደግሞ ከድርድሩ መሰረታዊ መርህ ባፈነገጠ መልኩ ኢትዮጵያ ኢፍትሀዊ የውሀ አጠቃቀም ስምምነትን እንድትቀበል በእጅ አዙር ጫና ለማሳረፍ እየጣረች ትገኛለች፡፡

የግብጻውያን ጫና እንዲሁም ዛቻና ፉከራው እየጨመረ የመጣው የህዳሴ ግድብ ግንባታ እየተፋጠነ መሄዱ በተለይም ከጥቂት ሳምንታት በኋላ በሁለት ተርባይኖች አማካኝነት ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት የሚያስችለውን ውሀ መያዝ የሚጀምር በመሆኑ ነው፡፡ ግብጽ በአንድ በኩል በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መደራደር  በሌላም በኩል የግድቡን ግንባታ ከግብ እንዳይደርስ ለማድረግ የተለያዩ ጫናዎች በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡

ከግብጽ ቀጥተኛ ጫና በተጨማሪ የአሜሪካ መንግስት በተለያየ ጊዜያት የግብጽን መንግስት በመወገን በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር  ታስበው  የሚያወጣቸው መግለጫዎችና ማስፈራሪያዎች  በሶስቱ አገራት መካከል እየተካሄደ ያለውን ድርድር መፍትሄ አምጪ ከመሆን ይልቅ የተወሳሰበ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

ግብጽ ባሁኑ ወቅት በአንድ በኩል የአሜሪካን መንግስት እና የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ም/ቤት በጉዳዩ እንዲገቡ ስትማጸን ትታያለች በሌላ በኩል  ከድርድሩ መንፈስ ወጣ ባለ ሁኔታ ነገሩን በማክረር ወደ ግጭት የማምራት አዝማሚያ እያሳየች ነው፡፡የዚህ አቋሟ ማጠንጠኛ ደግሞ የውሀ ድርሻየን አትንኩብኝ የሚለው የሞኝ ለቅሶ ነው፡፡

ግብጽ፤ ሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ በቅኝ ግዛት ውል ካልተዳደርን  በሚል ግትር አቋሟ የፀናች ትመስላለች ፡፡ለዚህም ነው የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ ድርድር  ከማካሄድ ይልቅ ከድርድሩ ባፈነገጠ መልኩ ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማትና አሜሪካንን  በመጠቀም የኢትዮጵያን እጅ ለማስጠምዘዝ እየተንቀሳቀሰች ያለችው፡፡

ግብፅ ፤ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ያለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ በቅኝ ግዛት ዘመን የተፈረመውን የውሃ ድርሻዬን ይቀንስብኛል በሚል በመቃወም ላይ ትገኛለች።

ግብፅ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሆና እንዲከበርላት የምትፈልገውና ሌሎች የተፋሰሱ ሀገራት በተለይም ኢትዮጵያ እንድትቀበለው የምትፈልገው የቅኝ ግዛት ዘመን የአባይ ውሃ ድርሻ ክፍፍል ስምምነትን ሲሆን ይህ ስምምነት በታላቋ ብሪታኒያ መካከል እ.ኤ.አ በ1929 የተፈረመ ነበር፡፡

ስምምነቱም በግብፅ እና በታላቋ ብሪታንያ መካከል የተካሄደ ሲሆን ብሪታኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ እና ሱዳንን በመወከል ነው ስምምነቱን የፈረመችው።

ስምምነቱም ላይ ለግብፅ   በወንዙ የመጠቀም ሙሉ መብት የሚሰጥ ሲሆን፥ በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነቡ   የግድብ እና የመስኖ ፕሮጀክቶችን የመፍቀድ ሙሉ ስልጣን ለግብፅ የሰጠ ነበር።

ሌላኛው ስምምነት የመጀመሪያውን ስምምነት መነሻ በማድረግ ግብፅ እና ሱዳን እ.ኤ.አ በ1959 የተፈራረሙት ሲሆን ከናይል ውሀ በዓመት 55 ነጥብ 5 ቢሊየን ክዩቢክ ሜትር ውሃ /66 በመቶ/ ለግብፅ ፣18 ነጥብ 5 ቢሊየን ክዩቢክ ሜትር ውሃ / 22 በመቶ/ ለሱዳን የመደበ ነገር ግን የውሀውን 86 በመቶ የምታበረክተውን ኢትዮጵያን ያላካተተ ኢ- ፍትሀዊና መቼም ቢሆን ተቀባይነት የማይኖረው ስምምነት ነበር፡፡

ይህን ስምምነት እንዲከበርላት አጥብቃ እንደምትሻ ግብጽ አሁንም በተለያዩ ድርድሮች ላይ ያንጸባረቀቻቸው አቋሞች ያመላክታሉ።ይሁንና ይህ ጉዳይ ፈጽሞ ተቀባይነት ሊኖረው እንደማይችል ስትረዳ ኢትዮጵያ ላይ ያልተገባ የፖለቲካና እና የዲፕሎማሲ ጫና ለማሳረፍ የተለያዩ ሀገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ለመጠቀም እየሞከረች ትገኛለች ፡፡

በቅርቡም ግብፅ  ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ጥያቄ አቅርባለች፡፡ግብጽ በሦስቱ አገራት መካከል እየተካሄ ያለውን ድርድር ወደጎን በመተው ለሁለተኛ ጊዜ ለፀጥታው ምክር ቤት ያቀረበችው ጥያቄም አግባብ እንዳልሆነና ኢትዮጵያ እየገነባች ያለችው ግድብ የታችኞቹን ተፋሰስ  አገራት እንደማይጎዳ ፣የሰላም እና ፀጥታ ስጋትም አለመሆኑን  ለምክር ቤቱ አስታውቃለች።

ኢትዮጵያ በኣባይ ወንዝ ላይ መጠነ ሰፊ የመስኖ ፕሮጀክቶችን አልገነባችም ያ ቢሆን ኖሮ  የግብጽ ቅሬታ ተገቢ ነው ማለት ይቻል ነበር፡፡ኢትዮጵያ የምትገነባው ግድብ በታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት ላይ ጉልህ  ጉዳት የማያደርስ   የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ነው፡፡ ግድቡ መገንባት ለግብጽም ሆነ ለሱዳን የሚኖረው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው፡፡ይሁንና  የግብጽ መንግስት  ፍላጎት  የአባይ ውሀን በበላይነት መያዝ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡

በሦስቱ አገራት መካከል እየተካሄደ ያለው ድርድር በውሀ ክፍፍል ሳይሆን በግድቡ የውሃ አሞላል ሂደት ላይ ሆኖ ሳለ የዓባይ ወንዝ መነሻ የሆነችውን ኢትዮጵያን ባገለለ መልኩ የተደረገን የቅኝ ግዛት ስምምነት እንደመደራደሪያ ሀሳብ ማቅረብም አግባብ አለመሆኑን መንግስት ለፀጥታው ምክር ቤት  አቋሙን ግልፅ አድርጓል።

ኢትዮጵያ በፍትሀዊ ተጠቃሚነት ላይ የምታደርገውን ድርድር የመቀጠል ፍላጎት ያላት ቢሆንም የትኛውንም የተፋሰሱ አገራት ጥቅም በማይጎዳ መልኩ ግድቡን ለማጠናቀቅ  ቁርጠኝነት ነች፡፡

ለግብጽ ጥቅም ሲባል ኢትዮጵያ አዲስ የቅኝ ግዛት ውል የግዴታ አሜን ብላ እንድትቀበል በእጅ አዙር በአሜሪካ በኩል ጫና መደረጉ አሜሪካ ለመካከለኛው ምሥራቅ ጥቅሟ በተለይ ለግብጽ ስትል  ረጅም ርቀት ልትሄድ እንደምትችል ማሳያ ነው፡፡

ግብጽ ከግጭት ይልቅ ትብብርን ብትመርጥ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ለምሰራቅ አፍሪካ የጋራ ብልጽግና  የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ ነው፡፡ በያዘችው ኢፍትሀዊ አቋም ፀንታ ግጭትን የምትመርጥ ከሆነ ግን ቀጠናውን ቀውስና ትርምስ ውስጥ እንደሚያስገባው አያጠራጥርም፡፡

አባይ በደጇ ለሚያልፈው ግብጽ ከፈጣሪ የተሰጣት ፀጋ ከሆነ የወንዙ መፈጠሪያ የሆነችው ሀገር ኢትዮጵያ እንድትራብ መፍቀድ የሚችል ሰብዓዊ ፍጡር ይኖራል ማለት ዘበት ነው፡፡

ጦርነት አማራጭ አይደለም ! ነገር ግን በታሪካችን ኢትዮጵያን ወሮ  የተሳካለት  ሀገር እንደሌለ ዓለም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከሱዳንም ሆነ ከግብፅ ጋር ወደ ጦርነት የመግባት ፍላጎት እንደሌላት ነገር ግን ግድቡን ከማጠናቀቅም ሆነ ውሀውን ከመሙላት የሚያግዳት  ነገር እንደሌለ  ማንም ሊያውቀው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

እኛ ኢትዮጵያውያን የጦርነትን አስከፊነት ከማንም በላይ የምንገነዘብ ህዝቦች በመሆናችን በየትኛውም ሀገር ላይ ጉዳት ሳናደርስ የውኃ ሀብታችንን ተጠቅመን ለማደግ የምንገነባውን የታላቁ ህደሴ ግድባችንን በፍጥነት ጨርሰን ከድህነት ለመውጣት የጀመርነውን ታሪካዊ ጉዞ ልናፋጥን ይገባል፡፡

ምንጭ፡- የታላቁ ህዳሴ/ግ/ግ/ህ/ተ/አ/ብ/ም/ጽ/ቤት

###

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.