የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቅ የገባነውን ቃል የምናድስበት ነው! - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቅ የገባነውን ቃል የምናድስበት ነው!

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የህዝቦችን እኩልነት፣ አብሮ የመኖርና የመቻቻል እሴቶቻችንን ከማጎልበት ባሻገር በአገራችን እየተመዘገበ ያለውን ዘርፈ ብዙ ዕድገት እድገት ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ የሚመክሩበት ነው።
ይህ በዓል የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች እርስ በርሳቸው እንዲተዋወቁ በማድረጉ በአገራችን የአብሮ መኖርና መቻቻል ባህል እንዲዳብር አድርጓል፡፡
በተለይም መጋቢት 24/2004 ዓ.ም የተከበረው አንደኛ ዓመት ክብረ በዓል ከኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ታሪካዊ ቁርኝት አለው፡፡በዚሁ ዕለት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዘቦች አንድ ስጦታ አበረከቱ፡፡ስጦታው ደግሞ ላበረከቱት አስተዋጽኦና በቀጣይ ለሚያደርጉት ድጋፍ አደራ ጭምር የያዘ ዋንጫ ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዘቦችም በፌዴሬሽን ም/ቤት አማካኝነት ዋንጫውን ከተረከቡ በኋላ የጋራ ፕሮጀክታቸው የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ እስኪጠናቀቅ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገቡ፡፡ ቃላቸውን በማክበርም ዋንጫው በክልሎቻቸው በተዘዋወረበት ወቅት የህዝባዊ ንቅናቄ እና የገቢ ማሰባሰብ ስራ ሲያከናውኑ ቆይተዋል፡፡
ይህ ዋንጫ በቤኒሻንጉል፣ አፋር፣ትግራይ፣ አማራ፣ኦሮሚያ፣ትግራይ ደቡብ፣ሶማሌ ክልሎች በመዘዋወር ከፍተኛ ገቢ ያስገኘ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 10 ክፍለ ከተሞች የገቢ ማሰባሰብና የህዝብ ንቅናቄ የመፍጠር ሥራ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሁሉም ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች አሻራ ያረፈበት ፕሮጀክት እንደመሆኑ መጠን ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር ለእኛ ኢትዮጵያዊያን የትብብራችንና የአንድነታችን ማሳያ ነው።
አገራችን ከ100 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ በማውጣት በራሷ አቅም እየገነባች ያለው ፕሮጀክት የአገራችንን ዕድገት ከማሳየቱም ባሻገር በህዝቡም ዘንድ በራሳችን አቅም ማደግ እንችላለን የሚል መንፈስ ፈጥሯል።
ይህ የኢትዮጵያ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች በእልህና በቁጭት እንዲሁም በላቀ ሀገራዊ አንድነት የጀመሩት ታላቁ የህዳሴ ግድብ  ግንባታው እየተፋጠነ ዛሬ ወደ መገባደዱ ደርሷል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ፤ በቦንድ ግዢ፣ በስጦታ፣በ8100A አጭር መልዕክት እና ቶምቦላ ሎተሪ በመሳሰሉት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮጀክቶች  ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረጋቸው ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት  ከ14 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማሰባሰብ ተችሏል፡፡
ግድቡን ከጎርፍና ደለል ከመከላከል አንጻር የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ባደረጉት ሠፊ ርብርብና ጥረት ከ40 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና የተፋሰስ ልማት ስራዎች አከናውነዋል፡፡
ይህ ታሪካዊ ግድብ በመንግስት ቁርጠኛ አመራር እና በኢትዮጵያ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያውን ጠንካራ ርብርብ በርካታ ፈተናዎችን አልፎ ዛሬ 76 በመቶ የግንባታ ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሀገራችን የህዳሴ ጉዞ መሰረት ከመሆኑም በተጨማሪ በህዝባችን ውስጥ ለዘመናት የዘለቀውን በዓባይ ወንዘ የመጠቀም ቁጭት በአስተማማኝ ሁኔታ የመለሰ በመሆኑ ለግድቡ ግንባታ መላው ህዝባችን ድጋፉን በከፍተኛ ሁኔታ በመስጠቱ በግድቡ መገንባትና አስፈላጊነት ላይ ብሔራዊ መግባባት ፈጥሯል።
የኢትዮጵያ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት ያደረጉት ሁለንተናዊ ድጋፍ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው፡፡ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን እኛ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እስኪጠናቀቅ የሚጠበቅብንን ድጋፍ ለማድረግ የገባነውን ቃል የምናድስበት ዕለት ናት፡፡

 

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.