ታላቁ የህዳሴ ግድብ ፤ ለቀጠናዊ ትብብር የሚኖረው ሚና - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ታላቁ የህዳሴ ግድብ ፤ ለቀጠናዊ ትብብር የሚኖረው ሚና

በአለማችን የውሃ ፖለቲካ ምሁራንን ቀልብ የሳበው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ምንም እንኳን በኢትዮጵያ እና በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት መካከል ጊዜያዊ የሆነ የሃሳብ ልዩነት በመፍጠር የሃሳብ ተቃርኖዎችን ይዞ ቢመጣም የግድቡ ግንባታ ለተፋሰሱ ሃገራት የረጅም ጊዜ ቀጠናዊ ትብብር ትልቅ ሚና እንደሚኖረው የዘርፉ ምሁራን ይገለፃሉ፡፡
በአለማችን የድንቃ ድንቅ መዝገብ ውስጥ ረጅሙ ወንዝ በመባል የሚታወቀው የናይል ወንዝ 11 የምስራቅ እና የሰሜን አፍሪካ ሀገራትን ድንበር የሚያቋርጥ ሲሆን በደቡብ ከታንዛኒያ እና በምስራቅ ከኢትዮጵያ ተነስቶ ወደ ሱዳንና ግብፅ መዳረሻ ካደረገ በኋላ ወደ ሚዲትራኒያን ባህር እንደሚገባ በብዙ መፃህፍት ዋቢ ተደርጓል፡፡
ምንም እንኳን የውሃ ተፋሰሱ 11 ሀገራትን ቢያካተትም የ1929ዓ.ም እና የ1959ዓ.ም /እ.አ.አ/ የቅጅ ግዛት ስምምነት መርህ መሰረት በማድረግ የውሃ አጠቃቀሙ በሁለት ሀገራት የበላይነት ተይዞ ረዘም ላለ ጊዜ ቆይቷል፡፡ ወንዙ ከሚያመነጨው አመታዊ የውሃ ፍሰት ውስጥ 84 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ወደ ታችኛው ተፋስስ ሀገራት የሚፈስ ሲሆን ግብፅ 66 በመቶ እና ሱዳን 22 በመቶውን እንደሚጠቀሙበትና  ቀሪው 12 በመቶ የሚሆነው ደሞ በትነት መልክ የሚባክን መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
የወንዞች ሁሉ አውራ ስለሆነው ዓባይና ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ የግድብ ግንባታ ብዙ ተብሏል፤ ብዙም ተጽፏል። ከናይል ወንዝ 86  በመቶ ውሀ የሚመነጨው ከኢትዮጵያ ሲሆን፣ ቀሪው 14 በመቶ ደግሞ ከነጭ አባይ የሚገኝ ነው ። ታዋቂው ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን “…አባይ አባይ…የሀገር አድባር…የውጭ ሲሳይ…” እያለ ቅኔ የተቀኘለት ዓባይ የኢትዮጵያን ለም አፈር ጠራርጎ እያጋዘ ለግብጽና ለሱዳን በረከት እንደሆነ ለዘመናት ፈሷል። ዓባይ ለግብፅ የባህላዊና ዘመናዊ የመስኖ ልማት ዋነኛ አውታር ሆኖ አገልግሏል፤ እያገለገለም ነው። በዚህም ግብጽ የተለያዩ አትክልትና የፍራፍሬ ምርቶችን ከራሷ አልፎ ለአለም ገበያ እያቀረበች የውጭ ምንዛሪ ቋቷን እየሞላች ትገኛለች። ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያዊው ግዮንን ተጠቅማ ሰው ሰራሽ ሀይቆችን ፈጥራ ከፍተኛ የዓሳ ምርት ታመርታለች፤ የቱሪስት መስህቦችም ባለቤት ነች ግብጽ።
በአንጻሩ አብዛኛው የሀገራችን አካባቢ በተለያዩ ምክንያት ተራቁቶ ለም አፈሩ በመከላቱ ሳቢያ በሚያጋጥመው የዝናብ እጥረት ለተደጋጋሚ ድርቅና ረሀብ ተጋላጭ እንድንሆን አድርጓል። ዝናብ ላይ ጥገኛ የሆነው ግብርናችንም ክፉኛ እየተፈተነም ይገኛል።ሀገራችን ኢትዮጵያ ወደ ታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ከሚሄደው የውሃ ክፍል ውስጥ 86 በመቶ እና ከአመታዊ የዝናብ ፍስት ደግሞ 95 በመቶ የሚሆነው ድርሻ ለወንዙ በማዋጣት ከተፋሰሱ ሃገራት በግምባር ቀደምትነት ትጠቀሳለች ፡፡
ባለፉት አስር አመታት በላይኛው ተፋስስ ሃገራት/ ለምሳሌ በኢትዮጵያ/ የተፈጠሩ መሰረታዊ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ለውጦች በወንዙ ለመልማት በሚደረጉ ፍላጎቶች እና ጥረቶች ከታችኛው ተፋስስ ሀገራት የቅኝ ግዛት ትርክቶች ጋር የሚቃረኑ ሆነዋል፡፡ የኢትዮጵያ በተፋሱ ሃገራት ላይ ያላት የፖለቲካ ተሰሚነት፣ ሀገር ውስጥ  የግብርና መዋዕለ ልማት መጨመር እና የአርቡ አለም ህዝባዊ ተቃውሞ ኢትዮጵያ ለጀመረችው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን በውሃው ዘርፍ የተሰማሩ ምሁራን ያስረዳሉ፡፡    
ሀገራችን ኢትዮጵያ በ2003ዓ.ም ወርሃ መጋቢት ላይ በይፋ ግንባታ መጀመሩን ያበሰረችዉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከመላዊ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በተጨማሪ በተፋሰሱ ሀገራት /ሱዳንን ጨምሮ/ የቦንድ ግዥ በማደረግ እና ስራዉን ለማቀላጠፍ የሚያግዙ የግንባታ መሳሪያ በማቅረብ ያደረጉት ድጋፍ በቀጠናው ለሚኖረው በጋራ የማደግ የትብብር መንፈስ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡   
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚከናወንበት ቦታ ለሱዳን ቅርብ መሆኑ እና በኢትዮጵያ በኩል በዋናነት ለሀይል ማመንጫ የሚውል በመሆኑ ሀገሪቱ ከቀጠናው ሃገራት ጋር የጀመረችውን የሀይል ሽያጭ በሰፊው ለማዳረስ የሚያግዝ በመሆኑ በቀጠናው የሚኖረውን የኦኮኖሚ ትብብር ማዕቀፍ ለማጠናከር ከፍተኛ አተዋፅኦ ያበረክታል፡፡   
በቀጣይ በተፋሰሱ ሀገራት በናይል ወንዝ ላይ ለሚነሱ የልማት ፍላጎቶች የታላቁ ህዳሴ ግድብ ትልቅ መነሻ ሆኖ በማገልገል ሀገራት ቀጠናዊ ትስስር የሚፈጥሩ የልማት ሃሳቦች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያግዙ ጋራ ዕቅዶች እንዲኖራቸው ድጋፍ ያደርጋል፡፡
ምንጭ፡- የታላቁ ህዳሴ/ግ/ግ/ህ/ተ/አ/ብ/ም/ጽ/ቤት

 

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.