ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ተወያዩ - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ተወያዩ

ቀን፡-ጥቅምት 11-2013

ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ተወያዩ፡፡
በስብሰባው ላይ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፣ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹክሪ እና የውሃ እና መስኖ ሚኒስቴር ሞሃመድ አብዱል አቴህ እንዲሁም የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የውሃ ሚኒስትር ተሳትፈዋል።
በቪዲዮ ኮንፈረንስ በተካሄደው ስብሰባ በህዳሴ ግድብ ውሃ አሞላል እና አለቃቀቅ እንዲሁም ወደ ስራ በሚገባበት የድርድር ማዕቀፍ ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡
ስብሰባው በደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስቴር እና የአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሰብሳቢነት ነው የተካሄደው፡፡
ሚኒስትሮቹ የሶስትዮሽ ድርድሩ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ሃሳብ የተለዋወጡ ሲሆን፥ በዚህ መሰረት የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ሙሌትና አመታዊ የውሃ አለቃቀቁ ላይ የተጀመረው ድርድር ማስቀጠል አስፈላጊነት ላይ መግባባት መደረሱን የውሃ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በስብሰባው የሱዳን ወገን የድርድሩ አካሄድ ካልተለወጠ በድርድሩ አልሳተፍም የሚል አቋም ያንጸባረቀ ቢሆንም የአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀ መንበር በሚቀጥሉት አስር ቀናት ለመሪዎች ሊቀርብ የሚችል ውጤት እንዲመዘገብ በማሳሰብ ስብሰባውን አጠቃለዋል፡፡
የስብሰባው ሊቀ መንበር በሆነችው ኢትዮጵያ ሰብሳቢነት ድርድሩ በቀጣይ ቀናት እንደሚቀጥልም ይጠበቃል፡፡
(ኤፍ.ቢ.ሲ)

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.