ህዝቡ አንድ በመሆንና የሀገሪቱን ጥቅም በማስጠበቅ የህዳሴ ግድብን ለማጠናቀቅ የበኩሉን መወጣት አለበት - የሃገር ሽማግሌዎች - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ህዝቡ አንድ በመሆንና የሀገሪቱን ጥቅም በማስጠበቅ የህዳሴ ግድብን ለማጠናቀቅ የበኩሉን መወጣት አለበት - የሃገር ሽማግሌዎች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህዝቡ ከምንጊዜውም በላይ አንድ በመሆንና የሀገሪቱን ጥቅም በማስጠበቅ የህዳሴን ግድብ ለማጠናቀቅ የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት አሉ የሃገር ሽማግሌዎች ።
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የሃገር ሽማግሌዎቹ ህብረተሰቡ በየአካባቢው አንድነቱን በማጠናከር ኢትዮጵያውያንን ተጠቃሚ የሚያደርገውን የህዳሴ ግድብ ለማጠናቀቅ የተጀመሩ ጠንካራ ተሳትፎዎችን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
ከህዳሴ ግድቡ ድጋፍ ጎን ለጎን ሃይማኖት እና ብሄርን ሽፋን አድርገው የሚፈጸሙ መከፋፈሎችን ወጣቱ በጥሞና ተገንዝቦ በአንድነት መመከት እንደሚገባው አሳስበዋል።
ግድቡን ዳር ለማድረስ ሁሉም አንድ ሆኖ መደገፍ አማራጭ የለሌለው ጉዳይ መሆኑን የሚያነሱት የሃገር ሽማግሌዎቹ፥ የሃገሪቱን ጥቅም አሳልፎ መስጠት እንደማይገባም ያነሳሉ፡፡
የውጭ ጥቅም በማራመድ መንግስት ላይ ጫና መፍጠር አይገባም ይህም ከአንድ ኢትዮጵያዊ የሚጠበቅ አደለምም ነው የሚሉት።
የግል ጥቅም ለማግኘት ከውጭ አካል ጋር በመመሳጠር የሃገርን ጥቅም አሳልፈው የሚሰጡትን ህዝቡ አላማቸውን ማክሸፍ እንዳለበት ተናግረዋል።
የህዳሴ ግድብ ከሃይል አልፎ ለግብርና ከፍ ያለ ሚና እንዳለው ያነሱት የሃገር ሽማገሌዎቹ የግድቡን ግንባታ መደገፍ ለነገ የማይባል ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።
በሀገር ጉዳይ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚል ካለ የሚጎዳው እራሱን መሆኑን በመጥቀስምስ ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነት ያስፈልጋል ብለዋል ።
ህዳሴ ግድብን በአንድነት ከመደገፍ ጎን ለጎን ወጣቱ የሀገሩን ሰላም የሚያስጠብቅበት ጊዜ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
አሁን ወጣቱ ከምንጊዜውም በላይ በማንነቱ በመከፋፈል ግጭት ለመፍጠር የሚታትሩ ጠላቶቹን ማጤን እንደሚገባውም አስገንዝበዋል።
በቤተ - እምነቶች ተመሳስለው በመግባት በሙስሊሙ ሙስሊም መስለው በክርስቲያኑም ክርስቲያን መስለው የሚንቀሳቀሱ አካላትን በትኩረት በመከታተል መመከት እንደሚገባም መክረዋል።
ሰላምን በማደፍረስ የህዳሴ ግድብ ከዳር እንዳይደርስ እና ሀገሪቱን ለማፈራረስ ከሚሰሩ ቡድኖች ወጣቱ አካባቢውን በመጠበቅ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ጠይቀዋል።
 
 

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.