የህዳሴ ግድብን የተመለከተው የሶስትዮሽ ስብሰባ የአፍሪካ ህብረት በጨመራቸው ባለሙያዎች ሚና ላይ ተወያየ - መነሻ - am
Nested Portlets
Asset Publisher
Statistics
× አድራሻ: ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስኩየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር
Web Content Search
Asset Publisher
የህዳሴ ግድብን የተመለከተው የሶስትዮሽ ስብሰባ የአፍሪካ ህብረት በጨመራቸው ባለሙያዎች ሚና ላይ ውይይት አድርጓል።
የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በበይነ መረብ በኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳን የውሃ ሚኒስትሮች መካከል የተካሄደውን ውይይት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።
በመግለጫው ላይ የቀጣይ የድርድር ሂደትና የጊዜ ሰሌዳ የውይይቱ ዋነኛ አጀንዳ እንደነበር አስታውቋል።
በውይይቱ ከሶስቱም ሀገራት ሁለት ሁለት ባለሙያዎች በመመደብ በቀጣይ ህብረቱ በሰየማቸው ባለሙያዎች ተጨማሪ ሚና ዙሪያ ተወያይተው ለውሃ ሚኒስትሮች እንዲያቀርቡ ከስምምነት መደረሱን ጠቅሷል።
ባለሙያዎቹ ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም ተወያይተው ሪፖርታቸውን በማግስቱ ጥቅምት ለሚኒስትሮቹ ለማቅረብ ተስማምተዋልም ነው ያለው።
በዛሬው ስብሰባ የሰስቱ ሃገራት የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር እና በሶስቱ ሃገራት የውጭ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ በተደረሰው የጋራ መግባባት መሰረት በድርድሩ ቀጣይ አካሄድና በጊዜ ሰሌዳው ዙሪያ ውይይት ተካሄዷል።
(ኤፍ ቢ ሲ)
Nested Portlets
Asset Publisher
መጣጥፎች
— 5 Items per Page