ከግድቡ ግንባታ እና ከፍትሃዊ የጋራ ተጠቃሚነት ዓላማችን ላፍታም ዝንፍ አንልም! - መነሻ - am

Nested Portlets

Asset Publisher

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት 11 ወራት ከ984 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ Fri, 17 Jun 2022

ታንዛኒያ ሕዳሴ ግድቡ ሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገለጸች Wed, 8 Jun 2022

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡ Wed, 8 Jun 2022

Statistics

× አድራሻቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ኢትዮጵያ.
× ግንባታዉ የተጀመረበት ጊዜ :2011 እ.ኤ.አ.
×ስፋት፡1,874 ስየር ኪሎ ሜትር
× የመያዝ አቅም: 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር

Asset Publisher

ከግድቡ ግንባታ እና ከፍትሃዊ የጋራ ተጠቃሚነት ዓላማችን ላፍታም ዝንፍ አንልም!

ውሃ ለሰው ልጅ በህይወት መኖር እጅግ አስፈላጊ እና ዋናው የህይወት መሰረት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለአያሌ ዘመናት ምንም ሳትጠቀምበት የኖረችውን የአባይ ወንዝ መጠቀም ለሀገሪቱ የህልውና፣ የሉዓላዊነት እና የመብት ጉዳይ ነው፡፡ ሃገሪቱ ህዝቦቿን ከድቅድቅ ጭለማ እና ካስከፊ ድህነት ለማውጣት ታላቁ የህዳሴ ግድብን ቀን ከሌት በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡ በዚህ ግድብ መላው ኢትዮጵያዊ በባለቤትነት ስሜት ከእለት ጉርሱ ከአመት ልብሱ ቀንሶ የገንዘብ፣ በዕውቀቱ ፣ በጉልበቱ ድጋፍ እያደረገ እና እየተሳተፈ ያለዉ ነገን ተስፋ አድርጎ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህ ግድብ የነገው ሃገር ተረካቢዎች ህጻናት ሳይቀሩ ቦንድ በመግዛት ድጋፋቸውን እያበረከቱ ሲሆን ያለማንም ብድር እና ድጋፍ ግንባታውን ወደ ማይቀለበስበት ወሳኝ ደረጃ ማድረስ ተችሏል፡፡
ኢትዮጵያውያን የአባይ ወንዝ ከፍተኛዉ ውሃ መጠን መነሻ ሁና እያለ ከታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት መርህ በማመን እየተደራደረች ያለችው፡፡ ባለፉት አስርት ዓመታት ለሰላማዊ መፍትሄ ትልቅ ስፍራ በመስጠት የጋራ ተጠቃሚነትን ባማከለ መልኩ በድርድር ስምምነት ላይ ለመድረስ ሁል ጊዜም በሯ ክፍት ነው፡፡
ይሁን እንጂ በሮችዋን ክፍት አድርጋ ለድርድር መቅረብዋ ማንንም በመፍራት ወይም የማንንም ልዩ ፈቃድ ለመጠየቅ ደጅ እየጠናች አለመሆኑ በግልጽ ሊታወቅ ይገባል፡፡በተፈጥሮ ወንዝዋ ማንም ላይ ጉልህ ጉዳት ሳታደርስ መጠቀም የህልውናዋም፣ የሉዓላዊነቷም፣ የማንነትዋም ጉዳይ ነው፡፡ ማንም ሀገር ወይም ታዋቂ ግለሰብ ተነስቶ ሀገሪቱን በማስፈራራት የታላቁ ህዳሴ ግድብን ግንባታ ለማስቆም የሚደረግ ጥረት ከሀገሪቱ መንግስት ጋር ብቻ ሳይሆን ከመላው ኢትዮጵያዊ እና የነገው ትውልድ ጋር የማይታረቅ ፀብ ውስጥ መግባት ነው፡፡ ግድቡን ለማፍረስ አይደለም ለሟጓተት የሚደረጉ ሴራዎች መላውን ኢትዮጵያዊ በአንድነት በማሰለፍ በበለጠ ወኔ እና እልህ ድጋፉን እንዲያጠናከር ከማድረግ በቀር ውጤት አልባ ነው፡፡
በመሆኑም ቀና አሳቢ አደራዳሪ መስለው ፍርደ-ገምድል ውሳኔ በማስተላለፍ ጫና ለመፍጠር ያደረጉት ጥረት ያልተሳካላቸው ፤ ዛሬ ደግሞ መላው ኢትዮጵያዊ እንደዓይን ብሌኑ የሚመለከተውን ግድብ "ሊፈርስ ይችላል!" የሚለዉ ንግግር ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያሳዘነ እና ለዓለም ሰላም፣ በተለይም ለመካከለኛው ምስራቅ ደህንነት እየሰራሁ ነው ከምትል ታላቅ

ሃገር መሪ የማይጠበቅ ንግግር ነው፡፡ ይህን ንግግር የተፋሰሱ ሀገራት እና አፍሪካውያን ግብጽን ጨምሮ በጋራ ሊያወግዙት የሚገባ ሲሆን የአፍሪካ ህብረት ችግሩን በድርድር ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት የሚያንኳስስ ነዉ፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአሜሪካውን አምባሳደር ጠርተው ማብራሪያ መጠየቃቸው አግባብነት ያለው የዲፕሎማሲ አካሄድ ነው፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩም ጽ/ቤት የሰጠው መግለጫ ሃቁን ያገናዘበና ጥልቅ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው፡፡ በመሆኑም ጽህፈት ቤታችን አድናቆቱን በዚህ አጋጣሚ ይገልጻል፡፡ ኢትዮጵያውያን መንግስት የወሰደውን የጥንቃቄ እርምጃዎች ልናደንቅ እና ከጎኑ ልንቆም እንጂ ልንጨነቅ አይገባም ፡፡ ይህ ወቅት ልዩነታችንን ወደ ጎን ትተን አንድነታችንን ልናጠናክር እና ግድባችንን ይበልጥኑ በመደገፍ ግንባታውን አፋጥነን መጨረስ መቻል እንዳለብን የሚያመላክት ፤ ይህ ንግግርም ኢትዮጵያውያን ከመቼውም ጊዜ የበለጠ እንድንነቃ የሚያደርገን "የማንቂያ ደውል!" ነው፡፡
ኢትዮጵያ በታሪኳ ማንንም የማትነካ ነገር ግን የቱንም ያህል ኃያል ይሁን ከየትም ይምጣ የተቃጣባትን ወረራ ህዝቦችዋ በጋራ ክንዳቸው በመመከት በነጻነት ኮርታ የኖረች ሀገር ናት፡፡ ዛሬም ቢሆን የሰንደቅ ዓላማ ፕሮጄክታችን እና የህዝቦች አንድነት ማህተም የሆነውን ታላቁ የህዳሴ ግድባችን የነጻነታችን እና ሉዓላዊነታችን መገለጫ በመሆኑ እስከመስዋእትነት ከፍለን እንጠብቀዋለን፡፡ለግድቡ ከዛሬ ቀደሙ በበለጠ በተለያየ መልኩ እየተደረገ ያለዉን ህዝባዊ ድጋፍ አጠናክሮ ግንባታውን በማጠናቀቅ፡ በግድባችን ላይ የሚቃጣውን ማንኛውንም ኃይል በተባበረና በተጋመደ ህብረ- ብሄራዊ ክንዳችን በመመከት የአድዋን ድል ለመድገም ዘግጁ እንደሆንን እንገልፃን፡፡

ጥቅምት 2013 ዓ/ም
ግድባችን የአንድነታችን እና የሉዓላዊነታችን መገለጫ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር

Nested Portlets

Asset Publisher

— 5 Items per Page
Showing 1 - 5 of 16 results.